Loading
Singer
በምድር ፡ ላይ ፡ ብዙዎች ፡ አማልክቶች ፡ ይኖራሉ እያንዳንዳቸው ፡ በሚያመልኳቸው ፡ ይበጃሉ/ይሰራሉ (፪x) ብቻውን ፡ የእኔ ፡ ምሥጋና ፡ የተገባ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ከእርሱና ፡ ለእርሱ ፡ የሆነው እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው አዝ፦ ሃሌሉያ (፰x) ክብር ፡ ለእግዚአብሔር እርሱ ፡ ፈጥሮ ፡ ሕያው ፡ እስትንፋስ ፡ የሰጣችሁ የእጁ ፡ ሥራዎች ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ያላችሁ (፪x) ድምጻችሁን ፡ ከፍ ፡ አድርጋችሁ ፡ በምሥጋና የሚገባውን ፡ ክብር ፡ ያግኝና ይክበር ፡ በምሥጋና አዝ፦ ሃሌሉያ (፰x) ክብር ፡ ለእግዚአብሔር የሰው ፡ ዘሮች ፡ በየአገራቱ ፡ ያላችሁ ልዩ ፡ ቀለም ፡ ልዩ ፡ ልዩ ፡ ሕዝቦች ፡ በቋንቋችሁ (፪x) ለሥሙ ፡ የሚገባውን ፡ ክብር ፡ አምጡ በቅድስናው ፡ ሥፍራ ፡ ስገዱ ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ በሉ ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ (ክብሩ) ፡ ነው (፫x) . (1) . ፡ አምላክ ፡ ለሆንከው ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ ነው (፪x)