Loading
Singer
በመጽሃፍ ፡ ቅዱስ ፡ ውስጥ ፡ አንድ ፡ እውነት ፡ አለ ። እግዚአብሔር ፡ አምልኮንና ፡ ምሥጋናን ፡ ይወዳል ። ግዑዛን ፡ ፍጥረታት ፡ እንኳን ፡ ይህን ፡ ተረድተው ፡ ቀንና ፡ ሌሊት ፡ ሳያቋርጡ ፡ ያመልኩታል ። የእጆቹ ፡ ሥራ ፡ የሆንንና ፡ ፍቅሩን ፡ ያየን ፡ እኛማ ፡ እንዴት... ቀን ፡ ለቀን ፡ ነገርን ፡ ታወጣለች ሌሊት ፡ ለሌሊቱ ፡ ቀትር ፡ ትናገራለች ድምጻቸውን ፡ ከቶ ፡ ሳያሰሙ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ሲያዜሙ እኔም ፡ ልቤ ፡ በዚህ ፡ ተደነቀ የምሥጋና ፡ ዜማ ፡ አፈለቀ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ (፬x) (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ (ክብር ፡ ለአንተ ፡ ኢየሱስ) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ (፪x) (ሃሌሉያ) ዓይኖቼን ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ አቀናለሁ እጆቼን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ አመልክሃለሁ በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ አመልክሃለሁ (፪x) ሠማያት ፡ ክብርህን ፡ ያሳየሉ እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ እያሉ ፡ ይናገራሉ ሰነፍ ፡ በልቡ ፡ አምላክ ፡ የለም ፡ ቢልም የዓለም ፡ ምስክር ፡ እራስህን ፡ አልተውክም የማይታየው ፡ ባሕሪህ ፡ ታይቷል ለዘለዓለም ፡ ኃይልህም ፡ ተገልጧል ሃሌሉያ ፡ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉያ ፀሐይም ፡ . (1) . ፡ ታወጣለች እስከ ፡ ምድር ፡ ዳርቻም ፡ ድረስ ፡ ታዞራታለህ ከዋክብርትም ፡ በሌ'ት ፡ የምትመራ የጨረቃን ፡ ብርሃን ፡ የምታበራ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ጌታ ፡ አምላክ ፡ ማነው በህዋ ፡ ላይ ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ ሃሌሉያ ፡ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉያ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ፡ (ሃሌሉያ) ሃሌ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ በሠማይና ፡ በምድር ፡ መካከል ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነህ ። እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ የለም ። በሠማይም ፡ የለም ፤ በምድርም ፡ የለም ። ታላቅነት ፡ ገናናነት ፣ ክብር ፣ ምሥጋና ፣ ባለጠግነት ፡ ሁሉ ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን ። አሜን ! ዓይኖቼን ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ አቀናለሁ እጆቼን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ አመልክሃለሁ በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ አመልክሃለሁ (፪x)