Loading
Singer
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ክብር ፡ በአርያም ፡ ክብር ፡ በሰማይ ፡ ክብር ፡ በምድር ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ለእግዚአብሔር በዙፋኑ ፡ ለነገሠው ፡ ክብር ፡ ለለበሰው በታላቅ ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ የሚኖረው ፡ የማይለወጠው ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ የሆነው በዘመናት ፡ ጸንቶ ፡ ያለው አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው የአባቱን ፡ ፈቃድ ፡ ብቻ ፡ የፈጸመው ፡ እግዚአብሔር ፡ በእርሱ ፡ ብቻ ፡ ደስ ፡ የሚለው የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ በላይ ፡ ያለው ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ወደ ፡ እውነት ፡ ሁሉ ፡ ለሚመራው እግዚአብሔርን ፡ ለሚገለጸው ፡ ለሚያከብረው ክብር ፡ ሁሉ ፡ የሚገባው ፡ ለመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ነው