Loading
Singer
አምላኬ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አድርግሃለሁ ስምህን ፡ ለዘላላም ፡ እባርካለሁ እጅግ ፡ የተመሰግንህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ነህ ለታላቅነትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የሌለው ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ርህሩህና ፡ መሐሪ ፡ ነው ከቁጣ ፡ የራቀ ፡ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ለሚታገሱት ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቸር ፡ ነው ምህረቱ ፡ ያምላካችን ፡ በስራው ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ነው በቃሎችህ ፡ አቤቱ ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ በስራህም ፡ በመንግድህ ፡ ሁሉ ፡ ጽድቅ ፡ ነህ ተስፋ ፡ ለሚያደርጉህ ፡ ሁሉ ፡ አንተ ፡ እጅህን ፡ ትከፍታለህ ሕይወት ፡ ላለውም ፡ ሁሉ ፡ መልካምን ፡ ታጠግባለህ መንግሥትህ ፡ የዘለዓለም ፡ መንግሥት ፡ ናት እግዚአብሔር ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ግዛት አቤቱ ፡ ስራህ ፡ ሁሉ ፡ አንተን ፡ ያመስግኑሃል ቅዱሳንህም ፡ ሁሉ ፡ አንተኑ ፡ ይባርኩሃል