Loading
Singer
ማስተዋልህ ፡ በሊቅ ፡ አትመረመርም እግዚአብሄር ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ማንም ፡ አላየህም በላይ ፡ በከፍታ ፡ በክብር ፡ ትኖራለህ በበረከትህም ፡ ምድርን ፡ ታጠግባለህ ባለጠግነትህ ፡ አይጐድልም ይፈቃል ፡ ይፈሳል ፡ ዘላለም (፪x) አዝ፦ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ይገባሀልና አምሣያ ፡ የሌለህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህና (፪x) የፊትህ ፡ ብርህን ፡ ከፀሐይ ፡ ይደምቃል ሰባቱን ፡ ከዋክብት ፡ በእጆችህ ፡ ይዘሀል አይኖችህ ፡ እንደ ፡ እሣት ፡ ነበልባሎች ፡ ናቸው የራስህም ፡ ፀጉር ፡ ከነጭም ፡ ነጭ ፡ ነው ማን ፡ መቆም ፡ ይችላል ፡ ካንተ ፡ ጋር አይቶ ፡ ነፍስ ፡ ማን ፡ ይቀርለታል (፪x) አዝ፦ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ይገባሀልና አምሣያ ፡ የሌለህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህና (፪x) መላዕክት ፡ በፍርሀት ፡ ወድቀው ፡ ይሰግዱልሀል ያምልኮአቸው ፡ ሽታ ፡ ቤትህን ፡ ሞልቶታል ክብርና ፡ ውዳሴ ፡ ምስጋና ፡ ይገባሀል እያሉ ፡ እራቱ ፡ እንስሶች ፡ ያከብሩሀል ሽማግሌዎች ፡ ወድቀው ፡ የሰግዱልሀል በፈቃድህ ፡ ሁሉን ፡ ፈጥረሀል እያሉ ፡ ክብራቸውን ፡ ይሰጡሀል አዝ፦ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ይገባሀልና አምሣያ ፡ የሌለህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህና (፪x)