Loading
Singer
ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ለንጉሡ ወደ ፡ ማደሪያው ፡ ይግባ ፡ ወደመቅደሱ (፪x) ክበር ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ በምሥጋና እጅግ ፡ ለተፈራው ፡ ለሆነው ፡ ገናና (፪x) በመቅደሱ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አሰማለሁ ፡ በተራዬ ከሚፈሩት ፡ ቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ እለዋለሁ ፡ ክበር በመቅደሱ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አሰማለሁ ፡ በተራዬ ከሚፈሩት ፡ ቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ እለዋለሁ ፡ አምላኬ ፡ ክበር ክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ክበር ክበር ፡ ለዘለዓለም ፡ ክበር ክበር ፡ ሁልጊዜ ፡ ክበር ክበር ፡ ለዘለዓለም ፡ ክበር የምህረት ፡ ደጁ ፡ ለእኔ ፡ ተከፍቶ አየሁ ፡ የንጉሥ ፡ ዘንግ ፡ ደግሞ ፡ ተዘርግቶ ከጨለማው ፡ ገዢ ፡ ነጥቆ ፡ አውጥቶ ወደ ፡ ፍቅሩ ፡ መንግሥት ፡ አስገባኝ ፡ ጐትቶ (፪x) ሃሌሉያ ፡ አሃ (፬x) ሃሌሉያ ፡ አሃሃ (፬x) በምህረቱ ፡ ገባሁ ፡ ማን ፡ ሊከለክለኝ ኢየሱስ ፡ ቤዛዬ ፡ አዳኝ ፡ ስለሆነኝ ቅዱሱ ፡ ባለበት ፡ በውስጠኛው ፡ ስፍራ አገልጋይ ፡ አደረገኝ ፡ ስሙን ፡ እንድጠራ (፪x) ምህረቱ ፡ ከቦኛል ፡ በቅዱስ ፡ ደሙ ፡ አንጽቶኛል ታዲያ ፡ ማነው ፡ የሚቃወመኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካጸደቀኝ ምህረቱ ፡ ከቦኛል ፡ በቅዱስ ፡ ደሙ ፡ አንጽቶኛል ታዲያ ፡ ማነው ፡ የሚኮንነኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካጸደቀኝ ሃሌሉያ ፡ አሃ (፬x) ሃሌሉያ ፡ አሃሃ (፬x) ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ኦሆሆ ሃሌሉያ ፡ አሃሃ (፬x)