Loading
Singer
አዝ፣ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ማለት ፡ ነው ፡ የሚያረካኝ እኔ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ሌላ ፡ ቃል ፡ አይበቃኝ (፪x) ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ወዳጄ ልልህ ፡ እወዳለሁ ፡ ባለችኝ ፡ ቋንቋዬ ፡ (አቅሜ) ዓለም ፡ ሳይፈጠር ፡ ተመስግኖ ፡ ኖሯል ዓለምም ፡ ተፈጥሮ ፡ እስካሁን ፡ ተመልኳል ትልቁም ፡ ትንሹም ፡ ገናና ፡ ብሎታል እኔም ፡ ደግሞ ፡ አሁን ፡ ያንኑ ፡ ልደጋግም አዝ፣ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ማለት ፡ ነው ፡ የሚያረካኝ እኔ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ሌላ ፡ ቃል ፡ አይበቃኝ (፪x) ፍልስፍና ፡ በዝቶ ፡ ዕውቀት ፡ ተከማችቶ ጥበብ ፡ በጥበብ ፡ ላይ ፡ ሲታይ ፡ ተደርቦ ቆም ፡ ብዬ ፡ አሰብኩት ፡ የፈጠረውን ሁሉንም ፡ አዋቁ ፡ ብልህ ፡ መሆኑን አዝ፣ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ማለት ፡ ነው ፡ የሚያረካኝ እኔ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ሌላ ፡ ቃል ፡ አይበቃኝ (፪x) የሊቅ ፡ ዕውቀት ፡ ቀርቶ ፡ የረቀቀውን መቼ ፡ ቀላል ፡ ሆነ ፡ የሰውስ ፡ ጥበብ? ሁሉን ፡ ለፈጠረ ፡ ለዚህ ፡ ድንቅ ፡ ጌታ ሃሌሉያ ፡ እንጂ ፡ ምን ፡ ሊባል ፡ ነው ፡ ታዲያ? አዝ፣ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ማለት ፡ ነው ፡ የሚያረካኝ እኔ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ሌላ ፡ ቃል ፡ አይበቃኝ (፪x)