Loading
Singer
"እሄዳለሁ ፡ ሃገሬ ፡ ጌታዬን ፡ አየዋለሁኝ ላየው ፡ ፊትለፊቱ" ሃገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ በሠማያት በጉ ፡ ብርሃኗ ፡ የሆነላት ፡ የሆነላት ሃገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ በሠማያት የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ያዘጋጃት (፫x) እንግዳ ፡ ነኝና ፡ አልሆንም ፡ ቤተኛ (፪x) ሃገሬ ፡ ሠማይ ፡ ነው ፡ በላይ ፡ ርስት ፡ አለኛ ፡ በላይ ፡ ቤት ፡ አለኛ ተዘጋጅቼ ፡ ልጠብቀው ፡ ቤቴን ፡ ሌት ፡ ተቀን ፡ ላሰናዳው ይመጣል ፡ ጌታ ፡ ይመጣል ፤ ይመጣል ፡ እርሱ ፡ ይመጣል (፪x) አሃሃሃ ፡ አልዘናጋም ፡ አሃሃሃ ፡ ጠፊውን ፡ አይቼ አሃሃሃ ፡ በላዬ ፡ ላከማች ፡ አሃሃሃ ፡ ልስራ ፡ ተግቼ አሃሃሃ ፡ እርሱ ፡ ይመጣል ፡ አሃሃሃ ፡ ወይ ፡ እሄዳለሁ አሃሃሃ ፡ እንደስራዬ ፡ አሃሃሃ ፡ እቀበላለሁ ዐይን ፡ ያላያት ፡ የሰው ፡ እጅ ፡ ያልሰራት ለልጆቹ ፡ ጌታ ፡ ያዘጋጃት ሃገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ በሠማይ (፪x) የቅዱሳን ፡ የጻድቃን ፡ ከተማ ቀኑ ፡ ቀርቧል ፡ ወደዚያ ፡ ልገባ ሃገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ በሠማይ (፪x) መታረት ፡ መራቆት ፡ መራብም ፡ ያልፍና ሰቆቃው ፡ ሃዘኑ ፡ ሁሉ ፡ ይረሳና ጌታዬን ፡ ፊትለፊት ፡ በክብር ፡ አያለሁ ናፍቆቴን ፡ ደስታዬን ፡ ያኔ ፡ እወጣለሁ ይመጣል ፡ ጌታ ፡ ይመጣል ይመጣል ፡ እርሱ ፡ ይመጣል (፪x) የፍጻሜው ፡ መለከት ፡ ይነፋል ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በክብር ፡ ይመጣል ሃገር ፡ አለን ፡ እኛስ ፡ በሠማይ (፪x) በቅጽበት ፡ ዐይን ፡ ሁሉ ፡ ይለወጥና እንሄዳለን ፡ ልንኖር ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ሃገር ፡ አለን ፡ እኛስ ፡ በሠማይ (፪x) የዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር ፡ አላፊ ፡ ጠፊ ፡ ነው ውበት ፡ ደም ፡ ግባትም ፡ ሁሉ ፡ ረጋፊ ፡ ነው ጌታዬ ፡ ሲመጣ ፡ እንዳየው ፡ ሳላፍር ሥጋዪን ፡ ልጐስም ፡ ልኑር ፡ ለእርሱ ፡ ክብር ይመጣል ፡ ጌታ ፡ ይመጣል ይመጣል ፡ እርሱ ፡ ይመጣል (፪x) እዚህ ፡ ነዋሪ ፡ አይደለሁም ፡ አይደለሁም እንግዳ ፡ ነኝ ፡ እኔ ቆይታዬ ፡ ያበቃና ፡ ይፈጸማል ፡ እሄዳለሁ ፡ ሃገሬ ሃገሬ ፡ በሠማይ ፡ ሃገሬ ሃገሬ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ሃገሬ ሃገሬ ፡ በሠማይ ፡ ሃገሬ ሃገሬ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ሃገሬ (፪x)