Loading
Singer
በጐህ ፡ ብርሃን ፡ ወደ ፡ ሆነላት ፡ ከተማ ላልመለስ ፡ ከልብ ፡ ወስኛለሁ ፡ በዓላማ እጓዛለሁ ፡ እሄዳለሁ ፡ ጠባቡን ፡ መንገድ ፡ ይዣለሁ በዘመኑ ፡ መጨረሻ ፡ ከአምላኬ ፡ ጋር ፡ እኖራለሁ የልጁን ፡ መልክ ፡ እንድመስል ፡ ተወስኖልኛል ከምድር ፡ ሕይወቴ ፡ ባሻገር ፡ ሰማይ ፡ ክብር ፡ ይጠብቀኛል ጊዜው ፡ ሲደርስ ፡ የሚገለጥ ፡ በእውነት ፡ የሚታይ በክርስቶስ ፡ የወረስኩት ፡ ሃገር ፡ አለኝ ፡ በሰማይ አዝ፦ ሃገር ፡ አለኝ ፡ በሰማይ ፡ ሃገር ፡ አለኝ (ሃገር ፡ አለኝ) እግዚአብሔር ፡ ያዘጋጀልኝ ፡ ሃገር ፡ አለኝ (ሃገር ፡ አለኝ) እርስት ፡ አለኝ ፡ በሰማይ ፡ እርስት ፡ አለኝ (እርስት ፡ አለኝ) እግዚአብሔር ፡ ያዘጋጀልኝ ፡ ሃገር ፡ አለኝ (ሃገር ፡ አለኝ) ከከፍታዬ ፡ ላይ ፡ በጭራሽ ፡ አልወርድም ወደፊት ፡ እያየሁ ፡ ወደኋላ ፡ አልሄድም ኃይልን ፡ በሚሰጠኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ በክርስቶስ ፡ ፀጋ ፡ በድል ፡ እጓዛለሁ ኢየሩሳሌም ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ኢየሩሳሌም ፡ እገባለሁ (፪x) ምንም ፡ አስቸጋሪ ፡ ቢሆን ፡ መውደቅ ፡ መነሳቱ ላይደክም ፡ ላይዝል ፡ ጉልበቴ ፡ ጌታ ፡ አድርጐኛል ፡ ብርቱ ጉዞው ፡ በድል ፡ ሲጠናቀቅ ፡ ህልሜ ፡ ግብ ፡ ሲመታ ከበጉ ፡ ጋር ፡ እኖራለሁ ፡ ፍፁም ፡ በሆነ ፡ ደስታ አዝ፦ ሃገር ፡ አለኝ ፡ በሰማይ ፡ ሃገር ፡ አለኝ (ሃገር ፡ አለኝ) እግዚአብሔር ፡ ያዘጋጀልኝ ፡ ሃገር ፡ አለኝ (ሃገር ፡ አለኝ) እርስት ፡ አለኝ ፡ በሰማይ ፡ እርስት ፡ አለኝ (እርስት ፡ አለኝ) እግዚአብሔር ፡ ያዘጋጀልኝ ፡ ሃገር ፡ አለኝ (ሃገር ፡ አለኝ) ሃገር ፡ አለኝ ፡ በሰማይ ፡ ሃገር ፡ አለኝ እግዚአብሔር ፡ ያዘጋጀልኝ ፡ ሃገር ፡ አለኝ