Loading
Singer
አዝ፦ በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ የሚኖር ሁሉን ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል (፬x) መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ መሽሸጊያዬ ፡ ነህ ከሌሊቱ ፡ ግርማ ፡ ድኛለሁ ጉያህ ፡ ስር ፡ ነኝ ፡ በአንተ ፡ አምልጫለሁ ከአደጋና ፡ ከቀትር ፡ ጋኔን አሳለፍከኝ ፡ ይዘኀው ፡ እጄን በእርሱ ፡ ተማምኖ ፡ ለሚመካበት አለልኝ ፡ ብሎ ፡ ለታመነበት ያወጣል ፡ እንጂ ፡ ከቶ ፡ እርሱ ፡ አይጥልም እንደሰው ፡ አይደል ፡ ፈጽሞ ፡ አይዋሽም በእጁ ፡ ቀርጾ ፡ እሱ ፡ ለያዘው ፡ የጠበቀ ፡ ዋስትና ፡ አለው (፪x) አዝ፦ በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ የሚኖር ሁሉን ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል (፬x) መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ መሽሸጊያዬ ፡ ነህ ከሌሊቱ ፡ ግርማ ፡ ድኛለሁ ጉያህ ፡ ስር ፡ ነኝ ፡ በአንተ ፡ አምልጫለሁ ከአደጋና ፡ ከቀትር ፡ ጋኔን አሳለፍከኝ ፡ ይዘኀው ፡ እጄን ከክንፍይ ፡ በታች ፡ ለተማመነ ሌላውን ፡ ትቶ ፡ እርሱ ፡ አለኝ ፡ ላለ ጽኑ ፡ መኩሪያ ፡ ነው ፡ የማይበገር ሁኔታን ፡ አይቶ ፡ የማይቀየር ጉያው ፡ አድርጐ ፡ አቅፎ ፡ ያሳልፋል ትቶ ፡ አይሸስም ፡ ይልቅ ፡ ያቀርባል (፪x) አዝ፦ በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ የሚኖር ሁሉን ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል (፬x) መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ መሽሸጊያዬ ፡ ነህ ከሌሊቱ ፡ ግርማ ፡ ድኛለሁ ጉያህ ፡ ስር ፡ ነኝ ፡ በአንተ ፡ አምልጫለሁ ከአደጋና ፡ ከቀትር ፡ ጋኔን አሳለፍከኝ ፡ ይዘኀው ፡ እጄን ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ ከሚያስፈራው ከጨለማው ፡ ገዢ ፡ ከማይራራው ጋርዶ ፡ ሸሽጐ ፡ ነፍሴን ፡ የአዳነው ልጁ ፡ ለሆኑት ፡ ደራሽ ፡ የሆነው ቢደገፉት ፡ የማያሳፍር አርፌያለሁ ፡ በእርሱ ፡ ጥላ ፡ ስር (፪x) አዝ፦ በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ የሚኖር ሁሉን ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል (፬x) መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ መሽሸጊያዬ ፡ ነህ ከሌሊቱ ፡ ግርማ ፡ ድኛለሁ ጉያህ ፡ ስር ፡ ነኝ ፡ በአንተ ፡ አምልጫለሁ ከአደጋና ፡ ከቀትር ፡ ጋኔን አሳለፍከኝ ፡ ይዘኀው ፡ እጄን