Loading
Singer
አበቃለት ፡ ብሎ ፡ ድንጋይ ፡ አትሞበት ዳግም ፡ እንዳይነሳ ፡ ሁሉን ፡ ዘጋግቶበት የእርሱ ፡ ነገር ፡ በቃ ፡ ከእንግዲህ ፡ በኋላ ትንሳኤ ፡ ዓይኖርም ፡ ምንም ፡ መፍትሄ ፡ መላ ደምድሞ ፡ ቁጭ ፡ ብሎ ፡ የበላይ ፡ ነኝ ፡ ሲል ድንገት ፡ ሳያስበው ፡ መጣበት ፡ ኃያል የሞት ፡ መውጊያን ፡ ሽሮ ፡ ጉድ ፡ ሰራው ፡ ጠላቴን ሕይወት ፡ ታወጀልን ፡ አንሞትም ፡ ሞት አንሞትም ፡ ሞትን ፤ አንሞትም ፡ ሞትን (፪x) አዝ፦ ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ነው (፪x) ጉድ ፡ አርጐ ፡ ተነሳ ሞትን ፡ አሸነፎ ፡ ኢየሱስ ፡ ተነሳ ያንን ፡ ክፉ ፡ ጉድ ፡ አደረገው ያንን ፡ ጨካኝ ፡ ጉድ ፡ አደረገው ሳትናኤልን ፡ ጉድ ፡ አደረገው ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ አደረገው ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ አደረገው የትንሳኤው ፡ ጌታ ፡ ሞትን ፡ አሸንፎ ኃይላትን ፡ አለቃን ፡ ሥልጣናትን ፡ ገፎ መቃብር ፡ አልያዘው ፡ ሁሉን ፡ ጥሶ ፡ ወጣ ለእኛም ፡ ተስፋን ፡ ሰጠን ፡ ደግሞ ፡ እንደሚመጣ ሰይጣንን ፡ ቀጥቅጦ ፡ ድልን ፡ ስላወጀ ለፍጥረት ፡ የእርቅ ፡ በር ፡ ድልድዩ ፡ ተበጀ በኢየሱስ ፡ ለአመንን ፡ አዲስ ፡ ኪዳን ፡ ሆነ አሮጌ ፡ አዳፋው ፡ ታሪክ ፡ ተከደነ ታሪክ ፡ ተከደነ ፤ ታሪክ ፡ ተከደነ (፪x) አዝ፦ ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ነው (፪x) ጉድ ፡ አርጐ ፡ ተነሳ ሞትን ፡ አሸነፎ ፡ ኢየሱስ ፡ ተነሳ ያንን ፡ ክፉ ፡ ጉድ ፡ አደረገው ያንን ፡ ጨካኝ ፡ ጉድ ፡ አደረገው ሳትናኤልን ፡ ጉድ ፡ አደረገው ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ አደረገው ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ አደረገው ያኔ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሁሉ ፡ ተፈጽሟል የእኔም ፡ ስራ ፡ ሁሉ ፡ በእዛ ፡ ሰዓት ፡ አልቋል የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ዘመን ፡ ለእኔ ማመኔ ፡ እርግጥ ፡ ነው ፡ በኢየሱስ ፡ መዳኔ ሞቴን ፡ በሞት ፡ ሽሮ ፡ ሕይወትን ፡ ለሰጠኝ ዘምርለታለሁ ፡ በእርሱ ፡ ደስ ፡ እያለኝ ሳልሰጋ ፡ እኖራለሁ ፡ ከአምላኬ ፡ ጋራ ስማ ፡ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ከቶ ፡ አንተን ፡ አልፈራ ከቶ ፡ አንተን ፡ አልፈራ ፤ ከቶ ፡ አንተን ፡ አልፈራ (፪x) አዝ፦ ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ነው (፪x) ጉድ ፡ አርጐ ፡ ተነሳ ሞትን ፡ አሸነፎ ፡ ኢየሱስ ፡ ተነሳ ያንን ፡ ክፉ ፡ ጉድ ፡ አደረገው ያንን ፡ ጨካኝ ፡ ጉድ ፡ አደረገው ሳትናኤልን ፡ ጉድ ፡ አደረገው ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ አደረገው ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ አደረገው