Loading
Singer
ጐልጐታ ፡ ትመስክር ፡ ቀራንዮ ፡ ትናገር የጌታ ፡ ኃይል ፡ ጣሩን ፡ የአኳሃኑን ፡ ነገር አዝ፦ ከዚህስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከኢየሱስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከአምላኬ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከጌታ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ነፍሱን ፡ ስለእኔ ፡ የሚያሰጥ ፡ መውደድ መስቀል ፡ አሸክሞ ፡ አስጐንብሶ ፡ የሚያስኬድ የጌታዬን ፡ ፍቅር ፡ ምን ፡ ይመጥነዋል ከምንም ፡ ከምንም ፡ ከምንም ፡ ይበልጣል አዝ፦ ከኢየሱስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከዚህስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከአምላኬ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከጌታ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም እንዴት ፡ እንዲወደኝ ፡ እኔ ፡ የማውቀው የተወጋ ፡ ጐኑን ፡ እሱን ፡ ሳየው ፡ ነው የእሾህ ፡ አክሊል ፡ አርጐ ፡ አንገቱን ፡ የደፋው እኔን ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ ስቄ ፡ እንድኖር ፡ ነው አዝ፦ ከዚህስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከኢየሱስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከጌታ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከአምላኬ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ደም ፡ ግባት ፡ ውበትን ፡ የሌለው ፡ ተባለ ስለበደሌ ፡ ሲል ፡ ደቀቀ ፡ ቆሰለ አፉን ፡ አልከፈተም ፡ አምላኬ ፡ ዝም ፡ አለ ሕመሜን ፡ ታመመ ፡ ደዌን ፡ ተቀበለ አዝ፦ ከዚህስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከኢየሱስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከአምላኬ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከጌታ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ሀዘኔን ፡ ምሬቴን ፡ በሰፍነጉ ፡ ሞልቶ ኢየሱሴ ፡ ጠጣልኝ ፡ ከሰማያት ፡ መጥቶ ሁሉን ፡ ጨርሶታል ፡ ምንም ፡ አላስቀረም ለኔ ፡ ያስተረፈው ፡ ኾምጣጤኮ ፡ የለም አዝ፦ ከዚህስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከዚህስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከአምላኬ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ከጌታ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ጐልጐታ ፡ ትመስክር ፡ ቀራንዮ ፡ ትናገር የጌታ ፡ ኃይል ፡ ጣሩን ፡ የአኳሃኑን ፡ ነገር