Loading
Singer
"የእረፍቴ ፡ የእረፍቴ ፡ ሰዓት (፫x) እፎይ ፡ ምልበት (፪x) ጊዜው ፡ ደረሰ ፡ ጌታ ፡ ሊገለጥ ሊያሳርፈኝ ፡ ልጁን ፡ ሊያስመልጥ ሊገላግለኝ ፡ ልጁን ፡ ሊያስመልጥ ደረሰ ፡ ጌዘው ፡ ደረሰ (፪x) ፡ ጌታ ፡ ሊገለጥ ሊያሳርፈኝ ፡ ልጁን ፡ ሊያስመልጥ (፪x)" የእረፍቴ ፡ ሰዓት ፡ እፎይ ፡ ምልበት ምድርን ፡ ትቼ ፡ የምሄድበት ጊዜው ፡ ደረሰ ፡ ጌታ ፡ ሊገለጥ ሊያሳርፈኝ ፡ ልጁን ፡ ሊያስመልጥ (፫x) አዝ፦ ደረሰ ፡ ጊዜው ፡ ደረሰ (፪x) ደረሰ ፡ ጌታ ፡ ሊመጣ እፎይ ፡ ብዬ ፡ ላርፍ ፡ ሁሌ ፡ በደስታ (፭x) ጽዮን ፡ አገሬ ፡ የተመኘሁሽ ሰዓቱ ፡ ደርሷል ፡ በዐይኔ ፡ ላይሽ ሁሉም ፡ ይጠራል ፡ ወደአምላኩ ጊዜው ፡ ያበቃል ፡ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ልኩ ለእኔስ ፡ መኖሪያዬ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ የዘለዓለም ፡ ቤቴ ፡ ሰማይ ፡ በአብ ፡ ቀኝ እኔስ ፡ ማረፊያዬ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ የዘለዓለም ፡ ቤቴ ፡ ሰማይ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ተስፋ ፡ እንደሌላቸው ፡ ምድር ፡ አፈር ፡ ማብቂያቸው ያልፋል ፡ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ምኞት ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ ኧረፍት ዛሬ ፡ ሰላምን ፡ ያጡ ፡ ሁሉም ፡ ወዴርሱ ፡ ይምጡ መጻቱ ፡ ጌታ ፡ ሊገለጥ ፡ ወገኔ ፡ ቶሎ ፡ ብለህ ፡ አምልጥ አዝ፦ ደረሰ ፡ ጊዜው ፡ ደረሰ (፪x) ደረሰ ፡ ጌታ ፡ ሊመጣ እፎይ ፡ ብዬ ፡ ላርፍ ፡ ሁሌ ፡ በደስታ (፭x) ፀሐይ ፡ ጨረቃ ፡ ከቶ ፡ የሌለበት በጉ ፡ ኢየሱስ ፡ የሚያበራበት ጽድቅና ፡ እውነት ፡ ወደሞላበት ደርሷል ፡ ሰዓቱ ፡ የምሄድበት በአዲሱ ፡ አገሬ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ሆኜ አመልከዋለሁ ፡ ከመጥፋት ፡ ድኜ አዝ፦ ደረሰ ፡ ጊዜው ፡ ደረሰ (፪x) ደረሰ ፡ ጌታ ፡ ሊመጣ እፎይ ፡ ብዬ ፡ ላርፍ ፡ ሁሌ ፡ በደስታ (፭x) እፎይ ፡ ብዬ ፡ ላርፍ ፡ ሁሌ ፡ በደስታ (፬x)