Loading
Singer
አዝ፦ ከእንቅልፌ ፡ ነቅቸ ፡ ዓይኔን ፡ እንደገለጥኩ ዓለም ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ራሴን ፡ ጠየቅሁ ዘገባው ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ ደግሞ ፡ የሚጠብቀኝ እስቲ ፡ ዜና ፡ ላዳምጥ ፡ ትንሽ ፡ ሬዲዮ ፡ አለኝ ርዕስ ፡ ዜናዎች ፡ ብሎ ፡ እንደጀመረ ፍርሃት ፡ ፍርሃት ፡ አለኝ ፡ ልቤ ፡ ተሸበረ ያው ፡ እንደጠበቅኩት ፡ መልካም ፡ ወሬ ፡ የለም የለቅሶ ፡ የሃዘን ፡ የስብራት ፡ የደም ጊዜው ፡ ጊዜው ፡ ጊዜው (፪x) የጊዜው ፡ ምልክት ፡ ወቅቱና ፡ ዘመኑ የሬዲዮ ፡ ዜና ፡ የማታው ፡ የቀኑ ያየነው ፡ በቲቪ ፡ የጋዜጣው ፡ ወሬ መልካም ፡ ቀን ፡ ተወልዷል ፡ ከትናንቱ ፡ ዛሬ ዋ ፡ ጊዜው ፡ ኦሆሆ ፡ ጊዜው ስንቱን ፡ አሳየን ፡ ጊዜው መስከረም ፡ አስራ ፡ አንድ ፡ ገና ፡ በማለዳ አይሮፕላን ፡ ጥሶ ፡ የህንጻ ፡ ግድግዳ በፍራቻ ፡ ሆነው ፡ አእላፍ ፡ እያዩ መንትዮቹ ፡ ህንጻዎች ፡ ፈራረሱ ፡ ጋዩ ልጆቹዋን፡ እባሕር ፡ ያሰጠመች ፡ እናት ጭካኔቅ ፡ ግፍዋ ፡ ሲተረክ ፡ በጠዋት ትምህርት ፡ ቤት ፡ ሰለተጋደሉት ዜናው ፡ ሲያነበንብ ፡ በአንክሮት ፡ ሰማሁት አዝ፦ ከእንቅልፌ ፡ ነቅቸ ፡ ዓይኔን ፡ እንደገለጥኩ ዓለም ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ራሴን ፡ ጠየቅሁ ዘገባው ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ ደግሞ ፡ የሚጠብቀኝ እስቲ ፡ ዜና ፡ ላዳምጥ ፡ ትንሽ ፡ ሬዲዮ ፡ አለኝ የሩዋንዳው ፡ እልቂት ፡ በሺ ፡ ዘጠና ፡ አራት በሰነበት ፡ ቂም ፡ በዘር ፡ ቁርሾ ፡ ማክንያት የዳርፉር ፡ እናቶች ፡ ዛሬም ፡ ደጅ ፡ ናቸው የበረሃ ፡ አቡዋራ ፡ እየገረፋቸው ፍልስጤም ፡ ከእስሬኤል ፡ ዛሬም ፡ እልታረቀ በመካከለኛው ፡ ምስራቅ ፡ ዛሬም ፡ ስንቱ ፡ አለቀ የሰው ፡ ፈንጂ ፡ ሆኖዋል ፡ ምድርን ፡ ያስጨንቃት ራሱ ፡ እንደጡዋፍ ፡ ነዶ ፡ አጥፍቶ ፡ ለማጥፋት አዝ፦ ከእንቅልፌ ፡ ነቅቸ ፡ ዓይኔን ፡ እንደገለጥኩ ዓለም ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ራሴን ፡ ጠየቅሁ ዘገባው ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ ደግሞ ፡ የሚጠብቀኝ እስቲ ፡ ዜና ፡ ላዳምጥ ፡ ትንሽ ፡ ሬዲዮ ፡ አለኝ የጦርነት ፡ የሁካታ ፡ ወሬ ፡ በዝቶ ዝናብ ፡ ጠፍቶ ፡ ምድር ፡ ደርቃ ፡ ችጋር ፡ ገብቶ ልጅ ፡ ከወለደች ፡ ባል ፡ ከሚስቱ ፡ ተከዳድቶ ገንዘብ ፡ ነግሶ ፡ መተማመን ፡ ከምድር ፡ ጠፍቶ ይህ ፡ ጊዜያዊ ፡ መኖርያችን ፡ ተውሳክ ፡ ቦታ ማብቂያው ፡ ቀርቧል ፡ ሊገለጥ ፡ ነው ፡ የድል ፡ ጌታ የምናየው ፡ የምንሰማው ፡ ይቀስቅሰን እንዘጋጅ ፡ ለምጽአቱ ፡ ለታላቅ ፡ ቀን