Loading
ጊዜው ፡ እጅግ ፡ ከባድና ፡ አሰቃቂ ፡ ጊዜ ፡ ነበር ፡ ኦሆ ከሰውነቱ ፡ የሚወጣው ፡ ላብ ፡ እና ፡ ደም ፡ ነጠብጣብ ፡ ነበር ፡ ኦሆ የጐልጐታው ፡ ታሪክማ ፡ ስንቱ ፡ ይወራ ፡ ስንቱ ፡ ይነግር ፡ ኦሆ ልረሳው ፡ ልዘነጋው ፡ እኔ ፡ አልችልም ፡ ይህንን ፡ ነገር እስቲ ፡ ላክብርህ ፡ እስቲ ፡ ላንግስ ወድሃልሁ ፡ ጌታ ፡ ያለልክ (፪x) የረሃቡ ፡ የጥማቱ ፡ የመብረዱ ፡ የመንቀጥቀጡ አቤት ፡ ጭንቅት ፡ አቤት ፡ ስቃይ ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ እኮ ፡ ለእኔ ፡ ነዉ እነሆ ፡ ክብር ፡ እነሆ ፡ አምልኮ እነሆ ፡ ስግደት ፡ ይገባሃል ፡ እኮ (፪x) ይገርማል ፡ ሥራህ ይገርማል ፡ ችሎታህ ይገርማል ፡ ፍቅርህ ይገርማል ፡ ማዳንህ ፡ ኦሆ ይገርማል ፡ ፍቅርህ (፪x) ያንን ፡ የሚያህል ፡ ትልቅ ፡ መስቀል ፡ ተሸክሞ ፡ ተራራውን ፡ ወጥቶ ተጨነቀ ፡ ተሰቃየ ፡ እንዲህ ፡ እንዲያ ፡ ተገባው እስቲ ፡ ላክብርህ ፡ እስቲ ፡ ልንበርከክ ወድሃልሁ ፡ ጌታ ፡ ያለልክ (፪x) ይገርማል ፡ ሥራህ ይገርማል ፡ ችሎታህ ይገርማል ፡ ፍቅርህ ይገርማል ፡ ማዳንህ ፡ ኦሆ ይገርማል ፡ ፍቅርህ (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.