Loading
Singer
አዝ፦ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስን ፡ እስካገኝ ሰላም ፡ አላየሁም ፡ እረፍት ፡ አልነበረኝ የመቅብዝበዝ ፡ ኑሮ ፡ ነበር ፡ የሰቀቀን ታሪክ ፡ ተለወጠ ፡ ጌታን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን ሃይማኖት ፡ አለኝ ፡ ስል ፡ ስገበዝ ፡ ከርሜ (፪x) መጠውለጉን ፡ ሳላውቅ ፡ ቅጠል ፡ አገልድሜ (፪x) እርቃኔ ፡ ሲገለጥ ፡ እፍረት ፡ ያዘኝና (፪x) ወደ ፡ ጌታ ፡ ሮጥኩኝ ፡ መሃሪ ፡ ነውና አዝ፦ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስን ፡ እስካገኝ ሰላም ፡ አላየሁም ፡ እረፍት ፡ አልነበረኝ የመቅብዝበዝ ፡ ኑሮ ፡ ነበር ፡ የሰቀቀን ታሪክ ፡ ተለወጠ ፡ ጌታን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን ሰው ፡ በእህል ፡ አይጠግብም ፡ ውሃም ፡ አያረካው (፪x) የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ በፍቅር ፡ ካልነካው (፪x) ጤና ፡ ነኝ ፡ እያለ ፡ እራሱን ፡ ያስታል (፪x) ቀን ፡ ቀን ፡ በሳቀበት ፡ ማታ ፡ ያቃስታል አዝ፦ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስን ፡ እስካገኝ ሰላም ፡ አላየሁም ፡ እረፍት ፡ አልነበረኝ የመቅብዝበዝ ፡ ኑሮ ፡ ነበር ፡ የሰቀቀን ታሪክ ፡ ተለወጠ ፡ ጌታን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን ታሪክ ፡ ያለኝ ፡ ይመስል ፡ በከንቱ ፡ ስኮፈስ (፪x) ቀራንዮን ፡ ትቼ ፡ ታቹን ፡ ስመላለስ (፪x) ጫማዬን ፡ ስጨርስ ፡ በሸለቆ ፡ ድንጋይ (፪x) የመለኮት ፡ ጥሪ ፡ መጣልኝ ፡ ከሰማይ አዝ፦ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስን ፡ እስካገኝ ሰላም ፡ አላየሁም ፡ እረፍት ፡ አልነበረኝ የመቅብዝበዝ ፡ ኑሮ ፡ ነበር ፡ የሰቀቀን ታሪክ ፡ ተለወጠ ፡ ጌታን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን አልጋዬ ፡ ቆርቋሪ ፡ እንቅልፍ ፡ የማይሰጠኝ (፪x) ምንድነው ፡ እንደዚህ ፡ የሚያገላብጠኝ (፪x) እያልኩኝ ፡ ስመረር ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰ (፪x) የሰላም ፡ አሸንዳ ፡ በላዬ ፡ አፈሰሰ አዝ፦ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስን ፡ እስካገኝ ሰላም ፡ አላየሁም ፡ እረፍት ፡ አልነበረኝ የመቅብዝበዝ ፡ ኑሮ ፡ ነበር ፡ የሰቀቀን ታሪክ ፡ ተለወጠ ፡ ጌታን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን ቀኒቷም ፡ ትባረክ ፡ ጌታን ፡ ያየሁባት (፪x) ከዘመናት ፡ እስር ፡ የተፈታሁባት (፪x) የምስራች ፡ ያለኝም ፡ እርሱን ፡ ጌታ ፡ ይክፈለው (፪x) ጌታ ፡ እኔን ፡ ሲሸልም ፡ ለእርሱም ፡ አክሊል ፡ አለው (፪x) አዝ፦ የነፍሴን ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስን ፡ እስካገኝ ሰላም ፡ አላየሁም ፡ እረፍት ፡ አልነበረኝ የመቅብዝበዝ ፡ ኑሮ ፡ ነበር ፡ የሰቀቀን ታሪክ ፡ ተለወጠ ፡ ጌታን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን