Loading
Singer
አንድ ቀን ጌታዬን አየዋለሁኝ አክሊሌን ከእጁ እረከባለሁኝ አሜን አንድ ቀን ጌታዬን አየዋለሁኝ አክሊሌን ከእጁ እረከባለሁኝ ወንጌሉን እንድሰብክ ከልቤ ቆርጬ ጌታዬ አዞኛል እስከምድር ዳር ሮጬ ኢየሱስ ያድናል እያልኩኝ እናገራለሁ እሱ በሚያስታጥቀኝ ጉልበትም እቆማለሁ ...አዝ.. እነ ጳውሎስ ያወጁትን የመስቀሉን ስራ ወዮልኝ ባልናገር ለፍጥረት ባላወራ ወደ አህዛብ ሁሉ ሂድ ብሎኛል እሄዳለሁ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ነፍሳትን አመጣለሁ ...አዝ.. ብዙ ብዙ ሚስጥር ከጌታ ተምሬለሁ አዝመራው እንደነጣ እኔም አይቻለሁ ጠቦቶቹን ልጠብቅ በጎቹን ላሰማራ ኢየሱስ የእግዚብሔር ልጅ ሰጥቶኛል አደራ ...አዝ.. አንድ ቀን ሩጫዬ እንደሚያበቃ አውቃለሁ የሱሴን ፊት ለፊቱ ቆሜ አናግረዋለሁ ካባቱ ብሩካን ጋራ በቀኙ ያቆመኛል የተዘጋጀልኝን ሽልማት ይሰጠኛል ...አዝ..