Loading
Singer
አነባ ፡ ጌታዬ ፡ አፈር ፡ ላይ ፡ ተደፍቶ የወደቀበትን ፡ ጭንቀት ፡ ተመልክቶ ጌታዬ ፡ ተጨንቆ ፡ አባዬ ፡ ሆይ ፡ አለ አጋዥ ፡ አልተገኘም ፡ ለጌታ ፡ የዋለ መስቀል ፡ ተሸክሞ ፡ ትከሻው ፡ ተላጠ ግርፋቱ ፡ በዛ ፡ ገላው ፡ ተመለጠ ራቁቱን ፡ ደም ፡ ሲያፈስ ፡ በቀራንዮ ፡ ዋለ አንገቱ ፡ ደፋ ፡ ሲል ፡ እዳ ፡ ተከፈለ አዝ:- ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ (፪x) ዝናን ፡ ከበሬታን ፡ ሞገስን ፡ በሥጋ ሊያገኝ ፡ ወዶ ፡ ነፍሱን ፡ ከአለም ፡ ከሚያስጠጋ ይሻላል ፡ ጭንጋፉ ፡ ውዳቂ ፡ እኔን ፡ መሳይ በስጋው ፡ ተንቆ ፡ በእምነት ፡ ጌታን ፡ የሚያይ<፪> ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ (፪x) ማቅቆ ፡ በመከራ ፡ ጐስቋላ ፡ አካል ፡ ይዞ በረሃን ፡ የሚዘልቅ ፡ ጌታን ፡ ተመርኩዞ ተሽማቆ ፡ ኑሮን ፡ ለጌታ ፡ ሲል ፡ ችሎ ያለፈን ፡ አየሁት ፡ አክሊል ፡ ተቀብሎ አዝ:- ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ (፪x) በሞቱ ፡ ሊመስለው ፡ ጌታን ፡ ተከትሎ ወድቆም ፡ የሚነሳ ፡ አልሸነፍ ፡ ብሎ ለጠላቱ ፡ ታግሎ ፡ የማታ ፡ የማታ ጌታው ፡ ምሎለታል ፡ እርሱ ፡ እንደሚረታ አዝ:- ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ (፬x)