Loading
Singer
አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል ሐዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከኔ ፡ ወስደሃል (፪x) ከታላላቆች ፡ ከአለቆች ፡ ጋራ ፊት ፡ ለፊት ፡ ቆሜ ፡ እኩል ፡ ላወራ ስለሆንክልኝ ፡ ግርማ ፡ ሞገሴ ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል ሐዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከኔ ፡ ወስደሃል (፪x) አድነኸኛል ፡ ከሰቆቃዬ በአንተ ፡ መጽናናት ፡ ደርቋል ፡ እንባዬ አቁመኸኛል ፡ በተራራ ፡ ላይ አብቅተኸኛል ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል ሐዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከኔ ፡ ወስደሃል (፪x) በአንተ ፡ ለምልሟል ፡ ምድረ ፡ በዳዬ በረከት ፡ ሞልቷል ፡ የሕይይወት ፡ ጓዳዬ ላይ ፡ ታች ፡ ከማለት ፡ ከሩጫ ፡ አርፌ መብላት ፡ ጀመርኩኝ ፡ እሸት ፡ ቀጥፌ አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል ሐዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከኔ ፡ ወስደሃል (፪x) ዛሬስ ፡ ጠላቴ ፡ ሥፍራውን ፡ ለቋል ከላይ ፡ የነበር ፡ ከእግሬ ፡ ሥር ፡ ወድቋል በአንተ ፡ ጀግንነት ፡ ነጻ ፡ ወጣሁኝ አንተ ፡ ስትከብር ፡ እኔም ፡ ከበርኩኝ አዝ፦ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁና እስኪ ፡ ልሰዋልህ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና እንባዬን ፡ ጠርገህ ፡ ማቄን ፡ ቀደሃል ሐዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከኔ ፡ ወስደሃል (፪x)