Loading
Singer
ማሰሮው ፡ ሲሰበር ፡ ድብቁ ፡ ብርሃን ፡ ይወጣል ስንዴው ፡ ሲበሰብስ ፡ ቡቃያው ፡ ብዙ ፡ ያፈራል ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ የተሰበረ ፡ ልብ ፡ ያሻኛል ድምፅህን ፡ እንድሰማ ፡ የተግሳጽ ፡ ይሁን ፡ ወይም ፡ የምክር በድንግዝግዝ ፡ ጊዜ ፡ ወድቄ ፡ እንዳልሰበር ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ የተከፈተ ፡ ጆሮ ፡ ያሻኛል አንተን ፡ ለመመልከት ፡ ሁልጊዜ ፡ በፊቴ ፡ ስትሄድ ወደ ፡ ቀጠሮአችን ፡ ቦታ ፡ በብርሃንህ ፡ እንድራመድ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ጤንነት ፡ ያለው ፡ ዓይን ፡ ያሻኛል ሰላምን ፡ ለማውራት ፡ የምሥራች ፡ ይዤ ፡ እንድሮጥ ፅድቅን ፡ ለተጠሙ ፡ ምንጩን ፡ እነሆ ፡ ለማለት ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ የሚራመዱ ፡ እግሮች ፡ ያሹኛል