Loading
Singer
የሆነው ፡ ነገር ፡ እርሱ ፡ የሚሆን ፡ ነው ፡ አሃ የተደረገው ፡ እርሱ ፡ የሚደረግ ፡ ነው ፡ አሃ (፪x) ከፀሐይ በታች ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ የለም እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ አይለመድም (፪x) ሰው ፡ በእውቀቱ ፡ ላይ ፡ ደርቦ ፡ እውቀትን ፡ ቢጨምር ይህም ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ከንቱ ለዓይኑ ፡ ያማረውን ፡ ከማድረግ ፡ ነፍሱን ፡ ባይከለክል ይህም ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ከንቱ ማረፍያዬ ፡ ብሎ ፡ ቤቶቹን ፡ ቢያሳምር ፡ ቢያስጌጥ ይህም ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ከንቱ ብርና ፡ ወርቅን ፡ አከማችቶ ፡ ለነገው ፡ ቢያስቀምጥ ይህም ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ከንቱ አዝ፦ ለሰው ፡ ከድካሙ ፡ በቀር ፡ ትርፉ ፡ ምንድን ፡ ነው ይልቅ ፡ በጉብዝናው ፡ ወራት ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው (፪x) ሳይደክሙ ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው ሳይጨልም ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው በሩ ፡ ሳይዘጋ ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው ነፍስም ፡ ሳትወጣ ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው አይ ፡ ጐበዝ ፡ የተባለው ፡ ሰው፡ አገር ፡ ሁሉ ፡ የሚያደንቀው ጥሮ ፡ ግሮ ፡ ያከማቸውን ፡ ጥሎት ፡ ሄደ ፡ ሳይበላው ፡ ሃብቱን ይሄም ፡ ከንቱ ፡ መድረሻው ፡ ምንድን ፡ ነው እድሜውን ፡ ሁሉ ፡ ጠፍሮት ፡ ስንፍናው እንደተባለ ፡ እንደቀረም ፡ መና ፡ እሱም ፡ ሄደ ፡ ሞት ፡ ቀደመውና ሳይደክሙ ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው ሳይጨልም ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው በሩ ፡ ሳይዘጋ ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው ነፍስም ፡ ሳትወጣ ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው አዝ፦ ለሰው ፡ ከድካሙ ፡ በቀር ፡ ትርፉ ፡ ምንድን ፡ ነው ይልቅ ፡ በጉብዝናው ፡ ወራት ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው (፪x)