Loading
የሰራኸውን ፡ ሳስተውለው ፡ ዞሬ አልጨርሰውም ፡ ሁሉንም ፡ ዘርዝሬ በፍቅር ፡ ቃላት ፡ እኔ ፡ ይህንን ፡ እላለሁ የወደደኝን ፡ እኔም ፡ እወደዋለሁ ጌታን ፡ እወደዋለሁ (፬x) አዝ፦አንደበቴን ፡ ቀብቶታል ጌታ ፡ ኑሮዬን ፡ ባርኮታል (፪x) ታዲያ ፡ ምኑ ፡ ዝም ፡ ያሰኘኝ ሁሌ ፡ ክብሩን ፡ እያሳየኝ (፪x) ክበር ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ እንጂ ንገሥ ፡ ልበል ፡ ንገሥ ፡ እንጂ ሌላ ፡ ቃላት ፡ ስለሌለኝ ሾሜሃለው ፡ ንገስልኝ ማነው ፡ የገመተ ፡ እዚህ ፡ ይደርሳል ፡ በሎ ጠላት ፡ ያለውን ፡ ወሬ ፡ ተቀብሎ ጌታ ፡ ሰው ፡ አረገኝ ፡ ጠላቴም ፡ አፈረ ማቄንም ፡ ቀደደ ፡ ቀንበሬን ፡ ሰበረ ጌታ ፡ ሰው ፡ አድርጐኛል (፬x) አዝ፦አንደበቴን ፡ ቀብቶታል ጌታ ፡ ኑሮዬን ፡ ባርኮታል (፪x) ታዲያ ፡ ምኑ ፡ ዝም ፡ ያሰኘኝ ሁሌ ፡ ክብሩን ፡ እያሳየኝ (፪x) ክበር ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ እንጂ ንገሥ ፡ ልበል ፡ ንገሥ ፡ እንጂ ሌላ ፡ ቃላት ፡ ስለሌለኝ ሾሜሃለው ፡ ንገስልኝ ባረከው ፡ ሕይወቴን ፡ ባረከው ፡ ኑሮዬን ስሾመው ፡ በላዬ ፡ ሳመልከው ፡ ጌታዬን በቀሪው ፡ ዘመኔም ፡ ጌታ ፡ ይንገስበት በሰጠኝም ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ይሰልጥንበት ጌታን ፡ እሾመዋለሁ (፪x) ጌታን ፡ አነግሰዋለሁ(፪x) አዝ፦አንደበቴን ፡ ቀብቶታል ጌታ ፡ ኑሮዬን ፡ ባርኮታል (፪x) ታዲያ ፡ ምኑ ፡ ዝም ፡ ያሰኘኝ ሁሌ ፡ ክብሩን ፡ እያሳየኝ (፪x) ክበር ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ እንጂ ንገሥ ፡ ልበል ፡ ንገሥ ፡ እንጂ ሌላ ፡ ቃላት ፡ ስለሌለኝ ሾሜሃለው ፡ ንገስልኝ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.