Loading
Singer
ምን ፡ ይሆን ፡ እድሌ ፡ ምን ፡ ይገጥመኝ ፡ ይሆን ብዬ ፡ አልጨነቅም ፡ ያልፈቀድከው ፡ ላይሆን የነፍሴ ፡ ጠባቂ ፡ እንዳይተኛም ፡ ካለው በአምላኬ ፡ ታምኜ ፡ ጉዞ ፡ እጀምራለሁ አምነዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ (፪x) ጌታን ፡ አምነዋለሁ አዝ:- በማለዳም ፡ እነሳለሁ አምላኬን ፡ አነግሠዋለሁ ምስጋናዬን ፡ እሰዋለሁ ውለታውን ፡ አስታውሰዋለሁ ጌታን ፡ አመልካለሁ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ እንደወደቀ ፡ እርጉም አስታዋሽ ፡ አጥቼ ፡ ለሞት ፡ አልተጣልኩም በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ብቻውን ፡ ያሰበኝ ለልቤ ፡ ማረፊያ ፡ አፍቃሪ ፡ አምላክ ፡ አለኝ አምላክ ፡ አለኝ ፡ አፍቃሪ ፡ አምላክ ፡ አለኝ (፪x) ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አለኝ አዝ:- በማለዳም ፡ እነሳለሁ አምላኬን ፡ አነግሠዋለሁ ምስጋናዬን ፡ እሰዋለሁ ውለታውን ፡ አስታውሰዋለሁ ጌታን ፡ አመልካለሁ የህልውናን ፡ ምንጭ ፡ ህልውናን ፡ ክደው ሞት ፡ የተዛመዱ ፡ ከመንገድህ ፡ ርቀው ባያውቁት ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ያደረግክላቸው ሊከፍሉት ፡ የማይችሉት ፡ ውለታ ፡ አለባቸው አለባቸው ፡ ውለታህ ፡ አለባቸው (፪x) ውለታህ ፡ አለባቸው አዝ:- በማለዳም ፡ እነሳለሁ አምላኬን ፡ አነግሠዋለሁ ምስጋናዬን ፡ እሰዋለሁ ውለታውን ፡ አስታውሰዋለሁ ጌታን ፡ አመልካለሁ ጀንበር ፡ ሊጠልቅ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ አልረበሽም እድል ፡ አመለጠኝ ፡ ብዬ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም አምላኬ ፡ እስካስቻለኝ ፡ ደረስ ፡ እጓዛለሁ በጐደለኝ ፡ ጌታ ፡ እንዲሞላው ፡ አውቃለሁ አመነዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አመነዋለሁ (፪x) ጌታን ፡ አምነዋለሁ አዝ:- በማለዳም ፡ እነሳለሁ አምላኬን ፡ አነግሠዋለሁ ምስጋናዬን ፡ እሰዋለሁ ውለታውን ፡ አስታውሰዋለሁ ጌታን ፡ አመልካለሁ