Loading
Singer
አዝ፦ ጌታቸው ፡ በመጣ ፡ ጊዜ ፡ ሲተጉ ፡ የሚያገኛቸው እነዚያ ፡ ባሮች ፡ ብጹኁን ፡ ናቸው (፪x) አስቀምጦ ፡ ያገለግላቸዋል ፡ በማዕዱ እኔንም ፡ አርገኝ ፡ ከእነርሱ ፡ እንደ ፡ አንዱ ቀጠሮ ፡ አፍራሽ ፡ የጊዜ ፡ ሌባ ፡ መምሸቱን ፡ አውቆ ፡ ቤቱ ፡ ማይገባ ከዘመን ፡ ኋላ ፡ ኋላ ፡ ተጎታች ፡ የሁሉም ፡ ጭራ ፡ ከሁሉም ፡ በታች ከቶ ፡ የማይገባኝ ፡ የህይወት ፡ ነገር ፡ እንዳልሆንብህ ፡ እንዳትቸገር እግሬ ፡ መራመድ ፡ እንዳያቅተው ፡ የሩቁን ፡ እንዳይ ፡ አይኔን ፡ ክፈተው አዝ፦ ጌታቸው ፡ በመጣ ፡ ጊዜ ፡ ሲተጉ ፡ የሚያገኛቸው እነዚያ ፡ ባሮች ፡ ብጹኁን ፡ ናቸው (፪x) አስቀምጦ ፡ ያገለግላቸዋል ፡ በማዕዱ እኔንም ፡ አርገኝ ፡ ከእነርሱ ፡ እንደ ፡ አንዱ ዓለም ፡ ስትከፋ ፡ ዘመን ፡ ሲጨልም ፡ ምርምር ፡ በዝቶ ፡ እምነት ፡ ሲደክም ፈጣሪን ፡ መፍራት ፡ ከምድር ፡ ሲጠፋ ፡ ፍጥረት ፡ ሲደገፍ ፡ በራሱ ፡ ተስፋ ቆይ ፡ ይደረሳል ፡ ማለት ፡ ይበቃል ፡ ነገን ፡ መኖሬን ፡ እግዚአብሄር ፡ ያውቃል ይልቅ ፡ ልነሳ ፡ ልክፈተው ፡ ደጁን ፡ መለከት ፡ ልንፋ ፡ ልንገር ፡ አዋጁን አዝ፦ ጌታቸው ፡ በመጣ ፡ ጊዜ ፡ ሲተጉ ፡ የሚያገኛቸው እነዚያ ፡ ባሮች ፡ ብጹኁን ፡ ናቸው (፪x) አስቀምጦ ፡ ያገለግላቸዋል ፡ በማዕዱ እኔንም ፡ አርገኝ ፡ ከእነርሱ ፡ እንደ ፡ አንዱ የመምጫውን ፡ ቀን ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ ያውቃል ፡ ጠብቁኝ ፡ ብሎ ፡ ያስጠነቅቃል የድል ፡ መለከት ፡ ሲነፋ ፡ ከላይ ፡ አንዷ ፡ በወፍጮ ፡ ሌላው ፡ በእርሻው ፡ ላይ ምጥ ፡ እርጉዝን ፡ ሴት ፡ እንደሚይዛት ፡ ድንገት ፡ ይሆናል ፡ የጌታ ፡ መምጣት በውጭ ፡ ጨለማ ፡ መጣል ፡ ይመጣል ፡ በተጠንቀቅ ፡ ግን ፡ መቆም ፡ ያዋጣል አዝ፦ ጌታቸው ፡ በመጣ ፡ ጊዜ ፡ ሲተጉ ፡ የሚያገኛቸው እነዚያ ፡ ባሮች ፡ ብጹኁን ፡ ናቸው (፪x) አስቀምጦ ፡ ያገለግላቸዋል ፡ በማዕዱ እኔንም ፡ አርገኝ ፡ ከእነርሱ ፡ እንደ ፡ አንዱ የማጽናኛ ፡ ቃል ፡ ለደከሙቱ ፡ የጥሪ ፡ ደወል ፡ ውጪ ፡ ላሉቱ በህይወት ፡ ማእበል ፡ ለሚንገላቱ ፡ የጸሎት ፡ ድጋፍ ፡ እንዲበረቱ አልነጋ ፡ ላለው ፡ ለጨለመበት ፡ መቆም ፡ እንድችል ፡ በፈረሰበት ባርከኝ ፡ በብዙ ፡ አታሳንሰኝ ፡ እየቆራረጥክ ፡ ለብዙ ፡ አድርሰኝ