Loading
Singer
ኃጢአት ፡ በዛብኝ ፡ ጉልበቴም ፡ ደከመ መራመድ ፡ አልቻልኩም ፡ መንገዴም ፡ ጨለመ ጠላቴም ፡ ይህን ፡ ሲያይ ፡ ሊሰብረኝ ፡ አለመ አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አትተወኝ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አትልቀቀኝ በጭንቀት ፡ ታስሬ ፡ እያለሁ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ መጥተህ ፡ አውጣኝ አንተን ፡ እያሳዘንኩ ፡ ደምህን ፡ እየረገምኩ ለልጆችህ ፡ ደግሞ ፡ እንቅፋት ፡ እየሆንኩ መላው ፡ ጠፋኝ ፡ ጌታ ፡ ግራ ፡ ተጋባሁኝ አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አትተወኝ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አትልቀቀኝ በጭንቀት ፡ ታስሬ ፡ እያለሁ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ መጥተህ ፡ አውጣኝ ቃልህን ፡ እንዳላነብ ፡ ፍላጐቴ ፡ ከድቶኝ ደግሞም ፡ እንዳልፀልይ ፡ ድካም ፡ ተጫጭኖኝ በጣሙን ፡ ዝያለሁ ፡ ተጐሳቁያለሁ አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አትተወኝ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አትልቀቀኝ በጭንቀት ፡ ታስሬ ፡ እያለሁ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ መጥተህ ፡ አውጣኝ በቅዱስ ፡ መንፈስህ ፡ ሕይወቴ ፡ ታትሞ በልጆችህ ፡ መሃል ፡ የእኔ ፡ መኖር ፡ ጠቅሞ ልገናኝህ ፡ አብቃኝ ፡ ሁሉ ፡ ተፈጽሞ አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አትተወኝ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አትልቀቀኝ በጭንቀት ፡ ታስሬ ፡ እያለሁ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ መጥተህ ፡ አውጣኝ መውደቅ ፡ በጥቂቱ ፡ መሞት ፡ በጥቂቱ መሆኑን ፡ አይቻለሁ ፡ ከመውደቅ ፡ ጠብቀኝ ማዕበሉ ፡ እንዳይጥለኝ ፡ ጐርፉም ፡ እንዳይወስደኝ አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አትተወኝ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አትልቀቀኝ በጭንቀት ፡ ታስሬ ፡ እያለሁ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ መጥተህ ፡ አውጣኝ