Loading
Singer
ጣል ፡ ጣል ፡ አታርጊው ፡ ኢየሱስን ፡ ውደጂው (፪x) ደግሞም ፡ አትናቂው ፡ ክብርን ፡ ለሱ ፡ ስጪው (፪x) ዓይንሽ ፡ ያረፈበት ፡ እሱ ፡ ያጠፋሻል (፪x) ተይ ፡ ተይ ፡ አትወላውይ ፡ ጌታ ፡ ይሻልሻል (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ ይሻልሻል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሻል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሻል ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሃል ነገ ፡ ዛሬ ፡ አትበል ፡ ኢየሱስን ፡ ተቀበል (፪x) የሚያባብልህን ፡ ዓለምን ፡ እምቢ ፡ በል (፪x) ከታሰርክበትም ፡ እርሱ ፡ ይፈታሃል (፪x) ቀረብ ፡ በል ፡ ተጠጋ ፡ ጌታ ፡ ይሻልሃል (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ ይሻልሻል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሻል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሻል ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሃል የሚያታልለውን ፡ የሱን ፡ ቃል ፡ አትስሚ (፪x) ይልቅስ ፡ ከአምላክሽ ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ተስማሚ (፪x) ሊሰርቅና ፡ ሊያድ ፡ ሊያጠፋሽ ፡ ነውና (፪x) ነይ ፡ ነይ ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ እሱን ፡ ተይውና (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ ይሻልሻል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሻል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሻል ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሃል እስኪ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ተስፋህ ፡ ምንድነው (፪x) ምንም ፡ ነገር ፡ የለ ፡ እስኪ ፡ አስበው (፪x) በዚህ ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ ሰብሰብ ፡ በልና (፪x) አረፍ ፡ በል ፡ ተቀመጥ ፡ ኢየሱስን ፡ ያዝና (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ ይሻልሃል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሃል፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሃል ኢየሱስ ፡ ይሻልሻል ፡ ኢየሱስ ፡ ይሻልሻል ፡ ጌታ ፡ ይሻልሻል