Loading
Singer
1. ሕይወት ፡ ተገላቢጦሽ ፡ ሲሆን ፡ ተመስገን ደስታ ፡ ለሓሰተኞች ፡ ስትሆን ፡ ተመስገን ሃዘን ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ሲበረታ ፡ ተመስገን ጉልበት ፡ በዝለትም ፡ ሲረታ ፡ ተመስገን በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን ስንደካክም ፡ ብርታት ፡ ሆነኸን ከኃይል ፡ ወደኃይል ፡ አሸጋገርኸን እዚህ ፡ ደርሰናል ፡ ተሸክመኸን (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ዕድል ፡ ፈንታ ፍጽም ፡ የማትረታ ስንደክም ፡ ስንበረታ በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን እናመሰግንሃለን 2. መከራ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ሲደርስብን ፡ ተመስገን ጠላትም ፡ ሲያጠፋን ፡ ሲዝትብን ፡ ተመስገን በአውሎ ፡ ንፋስ ፡ ስትናወጥ ፡ ታንኳችን ፡ ተመስገን መልስህ ፡ ስታጽናናን ፡ ጌታችን ፡ ተመስገን በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን ስንደካክም ፡ ብርታት ፡ ሆነኸን ከኃይል ፡ ወደኃይል ፡ አሸጋገርኸን እዚህ ፡ ደርሰናል ፡ ተሸክመኸን (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ዕድል ፡ ፈንታ ፍጽም ፡ የማትረታ ስንደክም ፡ ስንበረታ በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን እናመሰግንሃለን 3. ዘይትህ ፡ በእጅጉ ፡ ሞልቶ ፡ ሲፈስ ፡ ተመስገን ከእኛ ፡ አልፎ ፡ ሌሎችንም ፡ ሲፈውስ ፡ ተመስገን ዲያቢሎስ ፡ ሽንፈቱንም ፡ ሲጐነጭ ፡ ተመስገን እኛም እንደ እንድንቦሳ ስንፈነጭ ተመስገን በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን ስንደካክም ፡ ብርታት ፡ ሆነኸን ከኃይል ፡ ወደኃይል ፡ አሸጋገርኸን እዚህ ፡ ደርሰናል ፡ ተሸክመኸን (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ዕድል ፡ ፈንታ ፍጽም ፡ የማትረታ ስንደክም ፡ ስንበረታ በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን እናመሰግንሃለን 4. ወዳጅ ፡ ነው ፡ ያሉት ፡ ሁሉ ፡ ሲርቅ ፡ ተመስገን ከጠላት ፡ አብሮ ፡ እኛን ፡ ሲንቅ ፡ ተመስገን ሁሉ ፡ በጊዜው ፡ ሲፈራረቅ ፡ ተመስገን አንተ ፡ አለኸን ፡ በጭራሽ ፡ የማትርቅ ፡ ተመስገን በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን በድካማችን ፡ ብርታት ፡ ሆነኸን ከኃይል ፡ ወደኃይል ፡ አሸጋገርኸን እዚህ ፡ ደርሰናል ፡ ተሸክመኸን (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ የእኛ ፡ ዕድል ፡ ፈንታ ፍጽም ፡ የማትረታ ስንደክም ፡ ስንበረታ በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ አለህ ፡ አብረኸን እናመሰግንሃለን