Loading
Singer
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x) ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x) ቸርነትህ ፡ ምህረትህ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ ስለሚጠብቁኝ ፡ በመሆን ፡ ከጐኔ አልጠፋሁም ፡ ኢየሱስ ፡ አለሁኝ ፡ በቤትህ ስዘምር ፡ እኖራለሁ ፡ ለታላቁ ፡ ስምህ አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x) ጠላቴ ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ጦሩን ፡ ሲወረውር ከግድግዳ ፡ ጋርም ፡ እኔኑ ፡ ሊያጣብቅ ነገር ፡ ግን ፡ አልሆነም ፡ ምህረትህ ፡ ቀደመ የዲያብሎስ ፡ ሃሳብ ፡ እቅዱ ፡ ባከነ አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x) በምህረትህ ፡ ብዛት ፡ ቤትህ ፡ እገባለሁ አምልኮ ፡ ዝማሬ ፡ ስግደት ፡ እየሰጠሑ ገናም ፡ እኖራለሁ ፡ ስለምትጠብቀኝ እስከ ፡ ዓለም ፡ ፍጻሜ ፡ ሰለማትተወኝ አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x) አግዚአብሄር ፡ ታላቅ ፡ ባለብዙ ፡ ምህረት ልጅህ ፡ ስላረከኝ ፡ በብዙ ፡ ቸርነት እኔም ፡ በዝማሬ ፡ ምህረትህን ፡ አነግራለሁ እስከምትወስደኝ ፡ አገለግላለሁ አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x) በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ ሁሉን ፡ በምትችለው ባንተ ፡ ስለምኖር ፡ ምህረትህ ፡ በበዛው የሚያስፈራኝ ፡ የለም ፡ ከጠላትህ ፡ መንደር አንተ ፡ ስለጣልከልኝ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ ፡ ባሕር አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x) ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x) ልዑል ፡ ሆይ ፡ ምህረትህ ፡ እንዲሁም ፡ ጥበቃህ ደግሞም ፡ ቸርነትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝተዋል (፪x)