Loading
Singer
አዝ፦ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ አባት ፡ ተባረክ ፡ ወዳጅ ፡ ተባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ ጠራኸኝ ፡ ከዚህ ፡ ክፉ ፡ ዓለም ነፍሴን ፡ አዳንካት ፡ ዘለዓለም ከዚህ ፡ የበለጠ ፡ ደስታ ፡ ምንም ፡ የለም ይኸው ፡ ሞላልኝ ፡ ስለቴ ክበር ፡ ከፍ ፡ በል ፡ በህይወቴ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ይዋል ፡ መላው ፡ እኔነቴ አዝ፦ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ አባት ፡ ተባረክ ፡ ወዳጅ ፡ ተባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ በክቡር ፡ ደምህ ፡ አንጽተህ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ቀብተህ አገልጋይ ፡ አረግኸኝ ፡ ጸጋን ፡ ከላይ ፡ ሞልተህ ለስምህ ፡ ክብር ፡ ልዘምር ፡ በምሥጋና ፡ ላይ ፡ ልጨምር ላቆምኸኝ ፡ ላምላኬ ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ ክብር አዝ፦ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ አባት ፡ ተባረክ ፡ ወዳጅ ፡ ተባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ ጠላት ፡ ቢነሳ ፡ በአመጻ ፡ ቢወረውርም ፡ ፍላጻ ቆምኩኝ ፡ እስከዛሬ ፡ ከአንተ ፡ የተነሳ ክረምት ፡ ከበጋ ፡ አለፈ ፡ ቃልኪዳንህ ፡ መች ፡ ታጠፈ አንተን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ሲያይ ፡ ሁሉም ፡ ተሸነፈ አዝ፦ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ አባት ፡ ተባረክ ፡ ወዳጅ ፡ ተባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ የሶሪያ ፡ ንጉሥ ፡ ደማስቆ ሴራ ፡ ተንኮሉን ፡ ማን ፡ አውቆ አልሞ ፡ ነበር ፡ ሊይዘኝ ፡ አሾልቆ አንተ ፡ ግን ፡ አታጣ ፡ መላ ለባሪያህ ፡ ሆንኸኝ ፡ ከለላ አተምከው ፡ ዙሪያዬን ፡ በእሳት ፡ ሰረገላ አዝ፦ ጌታ ፡ ተባረክ ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ አባት ፡ ተባረክ ፡ ወዳጅ ፡ ተባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይንበርከክ