Loading
Singer
የደረቁ ፡ አጥንት ፡ ተስፋ ፡ የሌላቸው ለክብር ፡ ሆኑ ፡ ዛሬ ፡ ለምልመው ያለቀ ፡ ጉዳይ ፡ የሞተ ፡ ነገር ሕይወት ፡ ያገኛል ፡ ጌታ ፡ ሲናገር ጌታ ፡ ጌታ ፡ ሲናገር (፬x) እጄን ፡ ባፌ ፡ ላይ ፡ አስጭኖኛል ጌታ ፡ ለኔ ፡ ሲል ፡ ሁሉን ፡ ሆኗል ለመጣብኝ ፡ ሞት ፡ ራሱን ፡ ሰጥቶ ሰው ፡ አደረገኝ ፡ ለእኔ ፡ ሞቶ (፪x) ኧረ ፡ እንዴት ፡ ልርሳ ለእኔ ፡ የሆነው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ምነው ፡ ዘወትር ፡ ቃሎቼ ፡ በዝተው ጌታን ፡ ባመልከው ጌታን ፡ ባመልከው (፬x) ከፊቴ ፡ ይሰበር ፡ የብረት ፡ መዝጊያ ጠንካራ ፡ አላውቅም ፡ ከኢየሱስ ፡ ወዲያ አውቆ ፡ ይከፈታል ፡ ኃይልም ፡ አልጨርስ ሥሙ ፡ ሲጠራ ፡ የአዳኜ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ አዳኜ ፡ ኢየሱስ (፬x) እጄን ፡ ባፌ ፡ ላይ ፡ አስጭኖኛል ጌታ ፡ ለኔ ፡ ሲል ፡ ሁሉን ፡ ሆኗል ለመጣብኝ ፡ ሞት ፡ ራሱን ፡ ሰጥቶ ሰው ፡ አደረገኝ ፡ ለኔ ፡ ሞቶ (፪x) ኧረ ፡ እንዴት ፡ ልርሳ ለእኔ ፡ የሆነው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ምነው ፡ ዘወትር ፡ ቃሎቼ ፡ በዝተው ጌታን ፡ ባመልከው ጌታን ፡ ባመልከው (፬x) እኔስ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥ ፡ በሬን ፡ ዘግቼ እንባም ፡ አይወጣኝ ፡ ሞቱን ፡ ሰምቼ መቃብር ፡ ከፍቶ ፡ ድንጋይ ፡ ፈንቅሎ ተነሳ ፡ ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ተብሎ ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ተብሎ (፬x) እጄን ፡ ባፌ ፡ ላይ ፡ አስጭኖኛል ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ሲል ፡ ሁሉን ፡ ሆኗል ለመጣብኝ ፡ ሞት ፡ ራሱን ፡ ሰጥቶ ሰው ፡ አደረገኝ ፡ ለእኔ ፡ ሞቶ (፪x) ዝናህን ፡ ከሩቅ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ሥራ ሁሉም ፡ ሲያወራ ሰምቼ ፡ አልቀረሁ ፡ እንዲያው ፡ በወሬ አየሁህ ፡ ዛሬ አየሁህ ፡ ዛሬ (፬x) እጄን ፡ በአፌ ፡ ላይ ፡ አስጭኖኛል ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ሲል ፡ ሁሉን ፡ ሆኗል ለመጣብኝ ፡ ሞት ፡ ራሱን ፡ ሰጥቶ ሰው ፡ አደረገኝ ፡ ለእኔ ፡ ሞቶ (፬x)