Loading
Singer
አዝ፦ ጌታ ፡ ረዳቴ ፡ ነው ፡ በድካሜ መስቀሉን ፡ ይዣለሁ ፡ ተሸክሜ ልለየው ፡ ብሞክር ፡ ልክደው ፍቅሩ ፡ ግድ ፡ ይለኛል ፡ እንዳልተወው ሕይወቴ ፡ ሲደክም ፡ ሲዝልብኝ ረዳት ፡ የሌለኝ ፡ እኔን ፡ ሲመስለኝ ጌታ ፡ በክንዶቹ ፡ ያነሳኛል ደረቁን ፡ ሕይወቴን ፡ ያረካዋል አዝ፦ ጌታ ፡ ረዳቴ ፡ ነው ፡ በድካሜ መስቀሉን ፡ ይዣለሁ ፡ ተሸክሜ ልለየው ፡ ብሞክር ፡ ልክደው ፍቅሩ ፡ ግድ ፡ ይለኛል ፡ እንዳልተወው አንዴ ፡ በሸለቆ ፡ እንዲያ ፡ ሳለቅስ አንዴ ፡ በተራራ ፡ ስፈነጥዝ የመስቀሉን ፡ መንገድ ፡ ስለማመድ ብዙ ፡ ትምህርት ፡ አለው ፡ ልማር : ብወድ አዝ፦ ጌታ ፡ ረዳቴ ፡ ነው ፡ በድካሜ መስቀሉን ፡ ይዣለሁ ፡ ተሸክሜ ልለየው ፡ ብሞክር ፡ ልክደው ፍቅሩ ፡ ግድ ፡ ይለኛል ፡ እንዳልተወው እኔ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም ፡ እቆማለሁ የሕይወቴን ፡ መንገድ ፡ መርጫለሁ እደክማለሁ ፡ እንጂ ፡ ከቶ ፡ አልፈራም የሕይወትን ፡ እራስ ፡ አልክደውም አዝ፦ ጌታ ፡ ረዳቴ ፡ ነው ፡ በድካሜ መስቀሉን ፡ ይዣለሁ ፡ ተሸክሜ ልለየው ፡ ብሞክር ፡ ልክደው ፍቅሩ ፡ ግድ ፡ ይለኛል ፡ እንዳልተወው (፪x)