Loading
Singer
አለኝ ፡ ያልኩት ፡ ሁሉ ፡ በንፋስ ፡ ሲወሰድ ከመከራው ፡ ብዛት ፡ ብቻዬን ፡ ስሰደድ ተስፋዬ ፡ ተሟጦ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ሳለሁ እጁን ፡ የዘረጋ ፡ እንግዳ ፡ ሰው ፡ አየሁኝ አዝ:- ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ለእኔ ፡ የደረሰው (፪x) ቀንበር ፡ የከበደኝ ፡ ሸግም ፡ የበዛብኝ ያየኝ ፡ ሁሉ ፡ የጠላኝ ፡ ወዳጅ ፡ የራቀብኝ ተረስቼ ፡ ማንም ፡ የት ፡ ደረሰ ፡ አይለኝ አንድ ፡ ድምጽ ፡ ሰማሁ ፡ ና ፡ ልጄ ፡ የሚለኝ አዝ:- ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ለእኔ ፡ የደረሰው (፪x) የኀጢአት ፡ ባሪያ ፡ ሆኜ ፡ ደስታ ፡ ከእኔ ፡ ርቆ ከጭንቀቴ ፡ ብዛት ፡ እኔነቴ ፡ አልቆ ሌት ፡ ተቀን ፡ ፍራቻ ፡ ኑሮ ፡ ሆኖ ፡ እሮሮ ሞቶ ፡ ወስዶኝ ፡ ነበር ፡ ኢየሱስ ፡ ባይደርስ ፡ ኖሮ አዝ:- ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ለእኔ ፡ የደረሰው (፪x) ባወራው ፡ ባወራው ፡ አያልቅም ፡ ብናገር እንዴት ፡ እንዳወጣኝ ፡ ከዚያ ፡ ከሞት ፡ አገር እድሜ ፡ ቀጥሎልኝ ፡ እስካሁን ፡ አቆየኝ ሲዖል ፡ ቤቴ ፡ ነበር ፡ አምላኬ ፡ ባያየኝ አዝ:- ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ለእኔ ፡ የደረሰው (፪x)