Loading
Singer
ጌታ ፡ ለኔ ፡ ያድረከው ፡ ልቆጥረው ፡ አልችልም ፡ ወለታህ ፡ ብዙ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ ስለወደድ ፡ እወድሃለሁኝ ፡ አከብረሃለሁኝ ፡ ተመስገን ፡ እያልኩኝ ሳላውቅህ ፡ አውቀኸኝ ፡ ሳልወድህ ፡ ወድኸኝ በምረትህ ፡ ከበህ ፡ ቤትህ ፡ አኖርከኝ ከነፍሴ ፡ ምሥጋና ፡ ለአንተ ፡ እሰዋለሁ ምህረት ፡ ቸርነትህን ፡ እናገራለሁ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ አልታዘዝም ፡ ስል ፡ በደሌን ፡ ታግሰህ በፍቅርህ ፡ ገመድ ፡ ወዳንተ ፡ መልሰህ ስወድቅ ፡ አንስተኸኝ ፡ ስዝልም ፡ ደግፈህ እዚህ ፡ አደረሰከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ልበልህ የሚመስልህ ፡ የለም ፡ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ለዘለዓለምም ፡ የማትተወኝ በዘለዓለም ፡ ፍቅርህም ፡ የወደድከኝ ጌታ ፡ ኢየሱሴ ፡ የነፍሴ ፡ እረኛ ወዳጄ ፡ ነህ ፡ ለኔ ፡ የማትተኛ የማትለየኝ ፡ ስነቃም ፡ ስተኛ አትለዋውጥም ፡ ሁልጌዜ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ፈጥነህ ፡ ትደርሳለህ ፡ ስምህን ፡ ለሚጠሩህ ኢየሱስ ፡ አምባዬ ፡ ለኔ ፡ መጠጊያዬ ዞሮ ፡ መግቢያዬ ፡ ነህ ፡ መሸሸጊያዬ ከመከራ ፡ ሁሉ ፡ መዳኛዬ