Loading
Singer
ጌታ ፡ ለሕይወቴ ፡ አንተ ፡ መሪ ፡ ሁነህ ለኑሮዬም ፡ ጥላ ፡ ሃሩር ፡ እንዳይጐዳኝ እባክህ ፡ ሁንልኝ ፡ እኔ ፡ ደካማ ፡ ነኝ አንተ ፡ ግን ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ጸንተህ ፡ የምትገኝ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለልጅህ ፡ የምታውቅ ፡ አንተ ፡ ነህ የሚበጀኝንም ፡ ሁሉን ፡ አዘጋጅተህ ለእኔ ፡ ታስባለህ ፡ ትጠነቀቃለህ የማይጠቅመኝንም ፡ ወዲያ ፡ ትጥላለህ የልቤ ፡ ጓደኛ ፡ በአንተ ፡ እረካለሁ የምትሰጠኝንም ፡ እቀበልሃለሁ ሁሉን ፡ እንደወደድህ ፡ እንደ ፡ ፈቃድህ እንግዲህ ፡ አድርገው ፡ ደስ ፡ እንዳሰኘህ ከእንግዲህስ ፡ እኔ ፡ ምንም ፡ አልናገር ሰጥቼዋለሁኝ ፡ ሁሉን ፡ ለእግዚአብሔር በደስታም ፡ በሃዘን ፡ ተመስገን ፡ እያልሁኝ እርሱም ፡ ሚያደርገውን ፡ እኔ ፡ አያለሁኝ አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን