Loading
Singer
በእሳት ፡ ቁጥቋጦ ፡ የተገለጥከው የአብርሃም ፡ የይስሐቅ ፡ የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ነኝ ፡ ያልከው መርዛሙን ፡ እባብ ፡ በትር ፡ ያደረክ በመስኪን ፡ ነገር ፡ ባሕሩን ፡ የከፈልክ መርዙን ፡ አውጣልን ፡ ከበትራችን መድሃኒት ፡ አርገን ፡ ለምድራችን አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ የሱስ ፡ ሆይ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አትመጣም ፡ ወይ ጽድቅን ፡ ያደረግን ፡ እየመሰለን ባዶ ፡ ቅንአት ፡ እያቃጠለን የሕሊናን ፡ ድምጽ ፡ ተግሳጽን ፡ ንቆ እግራችን ፡ ሲሮጥ ፡ ወደ ፡ ደማስቆ በጽድቅ ፡ ጸሐይ ፡ ተገለጠልን የእይናችንን ፡ ቅርፊት ፡ ጣልልን አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ የሱስ ፡ ሆይ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አትመጣም ፡ ወይ ፍቅራችን ፡ ያንገት ፡ የለበጣ ፡ ነው ከአንተ ፡ አይደለም ፡ ከየት ፡ አመጣነው አንዱን ፡ ከሌላው ፡ እንለያለን ልብን ፡ አይደለም ፡ ልብስ ፡ እናያለን ልባችን ፡ ጨካኝ ፡ ለሰው ፡ አይራራ ዳስልንና ፡ ዓይናችን ፡ ይብራ አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ የሱስ ፡ ሆይ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አትመጣም ፡ ወይ የዕምነት ፡ አባቶች ፡ የቀደሙቱ ለፍቅር ፡ ኖረው ፡ ለፍቅር ፡ ሞቱ ታሪክ ፡ አንባቢ ፡ ሆነን ፡ ቀርተናል ከአንተ ፡ በስተቀ ፡ ማን ፡ ይችለናል የነሱ ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነህ እባክህ ፡ ጐብኘን ፡ ለስምህ ፡ ብለህ አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ የሱስ ፡ ሆይ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አትመጣም ፡ ወይ እሳትህ ፡ ቢነድ ፡ እንነጥራለን መዶሻ ፡ ብትልክ ፡ እንሰባበራለን ውኃ ፡ ብታፈስ ፡ እንጸዳለን ዝም ፡ ካልከን ፡ ግን ፡ እንጐዳለን ዛሬም ፡ ወዳንተ ፡ መጥተናልና ቤትህን ፡ ሙላ ፡ በክብር ፡ ዳመና አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ የሱስ ፡ ሆይ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አትመጣም ፡ ወይ