Loading
Singer
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ (፪x) ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን የእግዚአብሔር ፡ ቅባት ፡ ያለበት ቢባርክ ፡ የሚደርስለት ፡ ቢረግም ፡ የሚሆንለት ቢገስፅ ፡ የምንሰማው ፡ ቢቆጣን ፡ የምንፈራው ስንተኛ ፡ የሚያነቃን ፡ ስንሮጥ ፡ የሚያቆመን ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን (፪x) ፍቅርን ፡ ተቀብሎ ፡ የሚሰጥ ፡ የፍቅር ፡ መጋቢ ሀብታም ፡ ደሀ ፡ ብርቱ ፡ ደካማ ፡ ሁሉንም ፡ ሰብሳቢ በፍቅር ፡ በርህራሄ ፡ በትዕግስት ፡ መንጋህን ፡ ሚመራ የቆሰለ ፡ ፈዋሽ ፡ መድኃኒት ፡ ደራሽ ፡ በመከራ አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ (፪x) ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን የእግዚአብሔር ፡ ቅባት ፡ ያለበት ቢረግምም ፡ የሚደርስለት ፡ ቢባርክ ፡ የሚሆንለት ቢከፋን ፡ የምናዋየው ፡ ቢደክመን ፡ የምናርፍበት ብንቆስል ፡ የሚፈውሰን ፡ ብናዝን ፡ የሚያፅናናን ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን (፪x) ጩኸት ፡ አብዝተናል ፡ ውድድር ፡ እኔ ፡ እበልጥ ፡ እኔ ፡ እበልጥ ሁላችንም ፡ እኩል ፡ ሆነናል ፡ የለም ፡ መደማመጥ እረፉ ፡ የሚለን ፡ ተቆጪ ፡ እንደምን ፡ እንጣ ጌታሆይ ፡ እባክህ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ በቅባትህ ፡ አውጣ አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ (፪x) ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን የእግዚአብሔር ፡ ቅባት ፡ ያለበት ቢባርክ ፡ የሚደርስለት ፡ ቢረግምም ፡ የሚሆንለት ስንበድል ፡ የሚገስፀን ፡ ስንስት ፡ የሚመልሰን ስንጣላ ፡ የሚያስታርቀን ፡ ስንበተን ፡ ሚሰበስበን ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን (፪x) ቃሉ ፡ ከምድር ፡ ጠብ ፡ የማይል ፡ ቀንዱ ፡ ዘይት ፡ የሞላ ለተገፉ ፡ ድሆች ፡ ተሟጋች ፡ ጉቦ ፡ የማይበላ ለእውነት ፡ ኖሮ ፡ ለእውነት ፡ የሚሞት ፡ በዚህ ፡ ክፉ ፡ ዘመን ነገስታት ፡ ሲያጠፉ ፡ ሀይ ፡ የሚል ፡ ሳሙኤልን ፡ ስጠን አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ (፪x) ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን የእግዚአብሔር ፡ ቅባት ፡ ያለበት ቢባርክ ፡ የሚደርስለት ፡ ቢረግምም ፡ የሚሆንለት ስንፈራ ፡ ሚያደፋፍረን ፡ ስንጨነቅ ፡ አይዞ ፡ የሚለን ስንገፋ ፡ ሚሟገትልን ፡ ስንናቅ ፡ የሚቆምልን ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን (፪x) ቅድስት ፡ ከተማ ፡ ቅጥሯ ፡ ፈርሶ ፡ መቅደሱ ፡ ሲቃጠል በንጉስ ፡ ጮማ ፡ በወይን ፡ ጠጅ ፡ የማይቀማጠል ህዝብህን ፡ የሚያነሳሳ ፡ ቅጥሩን ፡ ለመጠገን ክብሩን ፡ ስለ ፡ ክብርህ ፡ የተወ ፡ ነህምያን ፡ ስጠን አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ (፪x) ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን የእግዚአብሔር ፡ ቅባት ፡ ያለበት ቢባርክ ፡ የሚደርስለት ፡ ቢረግምም ፡ የሚሆንለት ስንተኛ ፡ የሚያነቃን ፡ ስንሰንፍ ፡ የሚያተጋን ስንወድቅ ፡ የሚያነሳን ፡ ስንደክም ፡ የሚያበረታን ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን (፪x) ሙሴ ፡ ወይ ፡ ኢያሱ ፡ ኤልያስ ፡ ዼጥሮስ ፡ ቢሆን ፡ ዻውሎስ ብቻ ፡ ጌታችን ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ አስነሳ ፡ በመንፈስ አደባባይ ፡ ሞልቶ ፡ መፍሰሱ ፡ ምን ፡ አለው ፡ ቁም ፡ ነገር አንተ ፡ የቀባኸው ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ይበቃል ፡ ለሀገር አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ (፪x) ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን የእግዚአብሔር ፡ ቅባት ፡ ያለበት ቢባርክ ፡ የሚደርስለት ፡ ቢረግምም ፡ የሚሆንለት ጓዳችንን ፡ የምናሳየው ፡ ሚስጥራችንን ፡ የምናዋየው በፍቅር ፡ የሚገስፀን ፡ በትዕግስት ፡ የሚሸከመን ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ስጠን (፪x)