Loading
Singer
ስደክም ፡ እያደገፈ ፡ ስወድቅ ፡ አንስቶ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ተርቦ ፡ ስጠማ ፡ ተጠምቶ በስስታ ፡ እያየኝ ፡ ልጄ ፡ በርታ ፡ ሚለኝ ያ ፡ መልካሙ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በጣሙ ፡ ናፈቀኝ አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ትዝ ፡ አልከኝ ፤ ያደረክልኝ ፡ ውለታ ከዳሁህ ፡ ተታልዬ ፤ ትቀበለኝ ፡ እንደው ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልምጣ ሌሎቹም ፡ ክርስቲያኖች ፡ ሄዱ ፡ በጣም ፡ ተጉ በሕይወታቸው ፡ ግለው ፡ ወደ ፡ ድል ፡ ተጠጉ ለዓለም ፡ አገልጋይ ፡ ሆኜ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ ቀረኹኝ ያችን ፡ ኢየሩሳሌምን ፡ ከሩቅ ፡ እያየሁኝ አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ትዝ ፡ አልከኝ ፤ ያደረክልኝ ፡ ውለታ ከዳሁህ ፡ ተታልዬ ፤ ትቀበለኝ ፡ እንደው ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልምጣ ሰላምህ ፡ ከእኔ ፡ ሸሽቶ ፡ ጭንቀቴ ፡ እየገነነ ያመንኩት ፡ ሁሉ ፡ ከዳኝ ፡ የያዝኩት ፡ ተነነ ነፍሴ ፡ እንደተጐዳች ፡ ወዜም ፡ እንዳበረ ጌታዬን ፡ ባገኘው ፡ ኖሮ ፡ እነግረው ፡ ነበረ ብዬ ፡ ገና ፡ ስናገር ፤ ናልኝ ፡ ልጄ ፡ ሲል ፡ ሰማሁት በእግሩ ፡ ስር ፡ ተደፍቼ ፤ ቅዱስ ፡ ጌታዬን ፡ ወየሁ ፡ ማረኝ ፡ አልኩት ያለፈው ፡ ትምህርት ፡ ሆኖኝ ፡ የዓለም ፡ ጉስቁልና ጉልበቴን ፡ ላላስገዛ ፡ ለዓለም ፡ እንደገና ቃል ፡ ገባሁኝ ፡ በእርሱ ፡ ፊት ፡ ዳግም ፡ ላልለየው የእኔን ፡ ጉስቁልና ፡ ለአየ ፡ መቀጣጫ ፡ ይሁነው ለአንተ ፡ እገዛለሁኝ ፤ አንተ ፡ ነህ ፡ የነፍሴ ፡ ጌታ ብቸገር ፡ ብጐሳቆል ፤ እድሌ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ያለኸኝ ፡ አለኝታ (፪x)