Loading
Singer
አዝ፦ በቸርነትህ ፡ ዓመታትን ፡ ታቀናጃለህ በቸርነትህ ፡ ዘመናትን ፡ ታቀናጃለህ ጌታ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ (፪x) ምድራችንን ፡ ጐበኘሃት ፡ ምህረትን ፡ ለእርሷ ፡ አደረግህ ብልጽግናዋን ፡ አበዛህ ፡ ምግቧን ፡ አዘጋጅተህ ፡ ሰጥተህ . (1) . ፡ በማስተካከል ፡ እውነት ፡ እያለስለስካት ቡቃያውን ፡ በመባረክ ፡ መልካም ፡ ፍሬን ፡ አጠገብካት (፪x) አዝ፦ በቸርነትህ ፡ ዓመታትን ፡ ታቀናጃለህ በቸርነትህ ፡ ዘመናትን ፡ ታቀናጃለህ ጌታ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ (፪x) ከክብርህ ፡ ባለጠግነት ፡ ነፍሳችንን ፡ እያጠገብክ እስከ ፡ ሺ ፡ ትውልድ ፡ በሆነው ፡ በረከትህ ፡ እየባረክ ሁሉን ፡ ለእኛ ፡ ሰጥተኸናል ፡ የረገጥነውን ፡ ወርሰናል በስምህ ፡ ስልጣን ፡ በኃይልህ ፡ ሮሆቦት ፡ አሜን ፡ ሰርተናል (፪x) አዝ፦ በቸርነትህ ፡ ዓመታትን ፡ ታቀናጃለህ በቸርነትህ ፡ ዘመናትን ፡ ታቀናጃለህ ጌታ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ (፪x) የምድርን ፡ አፈር ፡ ባርከኸው ፡ ሰብልን ፡ ይሰጣል ፡ ዛሬ ጠግበን ፡ ረክተን ፡ እንኖራለን ፡ ለቅሷችን ፡ ሆኗል ፡ ዝማሬ ወራት ፡ አመት ፡ ዘመናትን ፡ ለልጆችህ ፡ ተሰጥተዋል ኤልሻዳይ ፡ ንጉሥ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሁሉን ፡ አቀዳጅተኸናል (፪x) አዝ፦ በቸርነትህ ፡ ዓመታትን ፡ ታቀናጃለህ በቸርነትህ ፡ ዘመናትን ፡ ታቀናጃለህ ጌታ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ (፪x) የምድረበዳ ፡ ተራሮች ፡ በመንፈስ ፡ እውነት ፡ ረክተዋል ኮረብቶችም ፡ በደስታ ፡ በስምህ ፡ ሀይልን ፡ ታጭቀዋል የማሰማሪያ ፡ ቦታዋች ፡ በመንጐቹ ፡ ውበት ፡ ለበሱ ሸለቆ ፡ እህል ፡ ተሞልቶ ፡ ክበር/ድመቅ ፡ ይልሃል ፡ ንጉሡ (፪x) አዝ፦ በቸርነትህ ፡ ዓመታትን ፡ ታቀናጃለህ በቸርነትህ ፡ ዘመናትን ፡ ታቀናጃለህ ጌታ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ (፪x)