Loading
Singer
አዝ፦ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳልኝ ፡ ክንዱ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳ ፡ ያ ፡ ክንዱ (፪x) ጠላቴ ፡ ሲከሰኝ ፡ አሃሃ ፡ ድካሜን ፡ ሲያሳየኝ ፡ ኦሆሆ ኃይል ፡ ሆነልኝ ፡ ለእኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ አገዘኝ (፪x) እራሴን ፡ ቀብቶ ፡ ኦሆሆ ፡ በመቅደሱ ፡ አቆመኝ ፡ አሃሃ እንደ ፡ መልካም ፡ እርሻ ፡ ውብ ፡ መዓዛ ፡ ሰጠኝ (፪x) አዝ፦ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳልኝ ፡ ክንዱ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳ ፡ ያ ፡ ክንዱ (፪x) በደሌን ፡ ኀጢአቴን ፡ አሃሃ ፡ በደሙ ፡ አጠበና ፡ ኦሆሆ ለእኔም ፡ አንደ ፡ ያዕቆብ ፡ ሥሜን ፡ ለወጠና ታሪክ ፡ ቃየረና የራሱ ፡ አደረገኝ ፡ ኦሆሆ ፡ በሥሙ ፡ ተጠራሁ ፡ አሃሃ በቀረው ፡ ዘመኔ ፡ ልኖር ፡ አስከብሬው ፡ እንድኖር አዝ፦ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳልኝ ፡ ክንዱ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳ ፡ ያ ፡ ክንዱ (፪x) ዝማሬ ፡ የሰማ ፡ አሃሃ ፡ በባዕድ ፡ አገር ፡ ላይ ፡ ኦሆሆ ሊያስጥለኝ ፡ ተነሳ ፡ ውዴን ፡ ከእጄ ፡ ላይ እኔን ፡ ከእርሱ ፡ ሊለይ እኔ ፡ ግን ፡ ተስፋዬን ፡ አሃሃ ፡ ላልረሳ ፡ ምያለሁ ፡ ኦሆሆ ደስታዬ ፡ በጌታ ፡ እንደሆነ ፡ አውቃለሁ ፡ ተደላድያለሁ አዝ፦ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳልኝ ፡ ክንዱ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳ ፡ ያ ፡ ክንዱ (፪x) የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ አሃሃ ፡ ዛሬም ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ኦሆሆ የተማመንኩበት ፡ ሥሙ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው እግሮቼን ፡ ጠብቆ ፡ ኦሆሆ ፡ ኃይልን ፡ አስታጥቆኛል ፡ አሃሃ በከፍታዎቹ ፡ በክብሩ ፡ አራምዶኛል ፡ በድል ፡ አቁሞኛል አዝ፦ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳልኝ ፡ ክንዱ ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ ስጠራው ከቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ ተነሳ ፡ ያ ፡ ክንዱ (፪x)