Loading
Singer
አምላኬ ፡ ነው ፡ የደገፈኝ ፡ እንዳልወድቅ ፡ በድካሜ በሃሩሩ ፡ ጥላ ፡ ሆኖ ፡ ሳይለየኝ ፡ ከአጠገቤ ከኋላዬ ፡ ሲከተለኝ ፡ እንቅፋቱ ፡ እንዳይጐዳኝ የጠላዬን ፡ ወጥመድ ፡ ሰብሮ ፡ መኖሪያዬ ፡ ሆነልኝ አሃ ፡ ሲከተለኝ አሃ ፡ ከኋላዬ አሃ ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው አሃ ፡ ከለላዬ አሃ ፡ ቀኑ ፡ ሲከፋ አሃ ፡ ሲጨልም አሃ ፡ ወንድም ፡ አለኝ አሃ ፡ አይዞህ ፡ የሚል ጌታ ፡ አለኝ (፲፪x) ቅጥር ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው ፡ እኔስ ፡ ያለፍኩት አላልፈው ፡ ነበር ፡ ባይኖረኝ ፡ አባት የትላንቱ ፡ ያን ፡ ጨለማ ይገርመኛል ፡ ኧረ ፡ እንዴት (፪x) ፡ እንዴት ፡ ጠፋ ሰባት ፡ እጥፍ ፡ የነደደው እሳት ፡ ጠፍቷል ፡ ጌታዬን (፪x) ፡ ላመስግነው ዋስትናዬ ፡ ሆኗል ፡ ለእኔ ፡ ጌታ (፬x) ከለላዬ ፡ ሆኗል ፡ ለእኔ ፡ ጌታ (፬x) የትላንቱን ፡ ያንን ፡ ወጀብ ፡ ቆም ፡ ብዬ ፡ ሳስበው የዛሬን ፡ ቀን ፡ ስላየልኝ ፡ ፀጥ ፡ ያረገው ፡ ጌታ ፡ ነው ለነገማ ፡ ዋስትና ፡ አለኝ ፡ ንፋስ ፡ ቢነፍስብኝ ፡ እላዬ ከእንግዲህማ ፡ ልቤ ፡ አይፈራም ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ በታንኳዬ አሃ ፡ ሲከተለኝ አሃ ፡ ከኋላዬ አሃ ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው አሃ ፡ ከለላዬ አሃ ፡ ቀኑ ፡ ሲከፋ አሃ ፡ ሲጨልም አሃ ፡ ወንድም ፡ አለኝ አሃ ፡ አይዞህ ፡ የሚል ጌታ ፡ አለኝ (፲፪x) ቅጥር ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው ፡ እኔስ ፡ ያለፍኩት አላልፈው ፡ ነበር ፡ ባይኖረኝ ፡ አባት የትላንቱ ፡ ያን ፡ ጨለማ ይገርመኛል ፡ ኧረ ፡ እንዴት (፪x) ፡ እንዴት ፡ ጠፋ ሰባት ፡ እጥፍ ፡ የነደደው እሳት ፡ ጠፍቷል ፡ ጌታዬን (፪x) ፡ ላመስግነው ዋስትናዬ ፡ ሆኗል ፡ ለእኔ ፡ ጌታ (፬x) ቤተኛዬ ፡ ሆኗል ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)