Loading
Singer
ሲሰማ ፡ ፉከራው ፡ ሽለላው ፡ የጠላቴ ፡ ወሬ (አሃሃ) ፡ የጠላቴ ፡ ወሬ (፪x) ሰው ፡ የሚተርፍ ፡ አይመስልም ፡ እኔ ፡ ግን ፡ አለሁ ፡ እስከዛሬ (አሃሃ) ፡ አለሁ ፡ እስከዛሬ (፪x) ተዉኝ ፡ ሌላ ፡ አልሰማም ፡ ቢፎክር ፡ ሁሉም ፡ ለጊዜው ፡ ነው (አሃሃ) ፡ ሁሉም ፡ ለጊዜው ፡ ነው (፪x) የሚያስፈራም ፡ ሆነ ፡ የሚያስደነግጠው ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (አሃሃ) ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x) ያረገውን ፡ አስቤ ፡ ከልቤ ፡ ኦ ፡ ከልቤ ማደሪያው ፡ ዙፋኑን ፡ ከብቤ ፡ ኦ ፡ ከብቤ ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ እላለሁ እኔማ ፡ መች ፡ ጠገብኩ ፡ ረካሁ (፪x) አለኝ ፡ ብዙ ፡ ሥራ ፡ ልነሳ ፡ ተረኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ (አሃሃ) ፡ ተረኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ (፪x) አትበሉ ፡ የልጅ ፡ ነገር ፡ እዩ ፡ እንጂ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከጐኔ (አሃሃ) ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከጐኔ (፪x) የሚመችም ፡ ባይሆን ፡ ቢከፋ ፡ ቢበዛም ፡ ውጊያዉ (አሃሃ)፡ ቢበዛም ፡ ውጊያዉ (፪x) እኔ ፡ አልመለስም ፡ ፈርቼ ፡ ጌታን ፡ ይዣለሁ (አሃሃ) ፡ ጌታን ፡ ይዣለሁ (፪x) ያረገውን ፡ አስቤ ፡ ከልቤ ፡ ኦ ፡ ከልቤ ማደሪያው ፡ ዙፋኑን ፡ ከብቤ ፡ ኦ ፡ ከብቤ ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ እላለሁ እኔማ ፡ መች ፡ ጠገብኩ ፡ ረካሁ ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ እላለሁ ለኔማ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የሆንከው የክብሩ ፡ ደመና ፡ መንፈሱ ፡ በላዬ ፡ አለፈ (አሃሃ)፡ በላዬ ፡ አለፈ (፪x) ጓዙን ፡ ጠቀለለ ፡ ሃዘኔ ፡ ባንተ ፡ ተገፈፈ (አሃሃ) ፡ ባንተ ፡ ተገፈፈ (፪x) የሰማዩ ፡ አዋጅ ፡ ዜናው ፡ ለኔ ፡ ምስራች ፡ ነው (አሃሃ) ፡ ለኔ ፡ ምስራች ፡ ነው (፪x) ምንም ፡ ነገር ፡ ባይኖር ፡ አምላኬ ፡ ከበቂ ፡ በላይ ፡ ነው (አሃሃ) ፡ ከበቂ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x) ያረገውን ፡ አስቤ ፡ ከልቤ ፡ ኦ ፡ ከልቤ ማደሪያውን ፡ ዙፋኑን ፡ ከብቤ ፡ ኦ ፡ ከብቤ ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ እላለሁ እኔማ ፡ መች ፡ ጠገብኩ ፡ ረካሁ (፪x) ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ እላለሁ ለኔማ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የሆንከው (፪x)