Loading
Singer
አዝ፦ ጌታ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ ኢየሱስ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ ፈጥኖ ፡ ደረሰና ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ ነፍሴን ፡ ከሚዋጋ ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ አሰላስላለሁ ፡ የጌታን ፡ በጐነት በእኔ ፡ ላይ ፡ ያለውን ፡ የአላማውን ፡ ፅናት ጌታ ፡ አስደንቆኛል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል ምህረቱን ፡ ልዘምር ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል ማዳኑን ፡ ልናገር ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ ኢየሱስ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ ፈጥኖ ፡ ደረሰና ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ ነፍሴን ፡ ከሚዋጋ ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ ሲጣሉ ፡ ብቻቸው ፡ ሲታዩ ፡ ግን ፡ በዙ ከእሳት ፡ የሚታደግ ፡ ማን ፡ ይሆን ፡ ጐበዙ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ የኃያላን ፡ ሃያል በምስሉ ፡ ላይሰግዱ ፡ ከሚጨክኑት ፡ ጋር ይቆማል ፡ እግዚአብሔር ፡ ስሙን ፡ ሊያስከብር ጌታ ፡ አስደንቆኛል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል ምህረቱን ፡ ልዘምር ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል ማዳኑን ፡ ላወራ ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል አዝ፦ ጌታ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ ኢየሱስ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ ፈጥኖ ፡ ደረሰና ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ ነፍሴን ፡ ከሚዋጋ ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ በአርጤክስስ ፡ ዘመን ፡ የሞት ፡ አዋጅ ፡ ወጣ አይሁድ ፡ እንዲወገድ ፡ ዝክሩ ፡ እንዲታጣ አዋጁን ፡ ለወጠው ፡ ሞትን ፡ ገለበጠው ከላይ ፡ ተፈርዶበት ፡ ጽዋውን ፡ ጨለጠው እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ስሙም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ጌታ ፡ አስደንቆኛል ፡ አመስግን ፡ ይለኛል ምህረቱን ፡ ልዘምር ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል ማዳኑን ፡ ልናገር ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ ኢየሱስ ፡ አበረታኸኝ ፡ አጠገቤ ፡ ቆሞ ፈጥኖ ፡ ደረሰና ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ ነፍሴን ፡ ከሚዋጋ ፡ ከክፉ ፡ ፊት ፡ ቀድሞ