Loading
Singer
የትኛው ፡ ወዳጅ ፡ ነው ፡ የትኛው ፡ አባት እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ ሳይደክም ፡ ሳይታክት ሊሸከም ፡ የሚወድ ፡ ከኃጥያት ፡ ከነክፋቴ ጌታ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ አየሁ ፡ ፍፁም ፡ አፍቃሪዬ ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፬x) ይገርማል ፡ መወደዴ ፡ ይገርማል ፡ መፈለጌ ይገርማል ፡ መመረጤ ፡ ይገርማል፡ መፈጠሬ ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፬x) ንጉሥ ፡ አዋጅ ፡ ቢያውጅ ፡ ጠላቴ ፡ ተጣድፎ እርግማን ፡ ሊረግመኝ ፡ ባላቅም ፡ ተቻኩሎ በለአም ፡ ግን ፡ ትእዛዝ ፡ ከላይ ፡ ተቀበለ አዋጅ ፡ ሻረ ፡ ጌታ ፡ ታሪክ ፡ ተለወጠ ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፪x) ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ (፪x) ይገርማል ፡ መታሰቤ ፡ በዓይኖቹ ፡ መታየቴ ገረመኝ ፡ እኔ ፡ መትረፌ ፡ በእጆቹ ፡ መያዜ ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፫x) የመኖሬን ፡ ሚስጢር ፡ ሳስብ ፡ ይደንቀኛል ዛሬ ፡ ላይ ፡ መቆሜ ፡ እጅግ ፡ ይገርመኛል አንተ ፡ ከላይ ፡ ሆነህ ፡ በዓይኖችህ ፡ አየኸኝ ምህረት ፡ ማፅናናትህ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ አሰኘኝ ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፪x) ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ (፪x) ይገርማል ፡ መወደዴ ፡ ይገርማል ፡ መፈለጌ ይገርማል ፡ መፈቀሬ ፡ ይገርማል ፡ መመረጤ ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ (፪x) ማንም ፡ ያልራራልኝ ፡ መንገድ ፡ የተጣልኩኝ በደም ፡ ተነክሬ ፡ ሞቴን ፡ የጠበቅሁኝ በእጅህ ፡ ታክሜ ፡ ድኜ ፡ ከህመሜ ከመሞት ፡ አምልጬ ፡ ገረመኝ ፡ መቆሜ ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፬x) ይገርማል ፡ ኧረ ፡ መትረፌ ፡ ከክፉዎች ፡ ማምለጤ ገረመኝ ፡ አሰራርህ ፡ ፍጥነትህ ፡ አደራረስህ ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፫x)