Loading
Singer
አቤቱ በስራህ - ስምህ የገነነ በሰማይ በምድር - የተመሰገነ፤ ያንተን ህልውና - የሚጠራጠሩ በእጆችህ ስራ - ከምክንያት አጠሩ። ገናና ነህ ዝነኛ የፍጥረት ምንጩ መገኛ ጅማሬህን አናውቀው - ፍፃሜህን አናውቀው በ'ድሜያችን በምናውቅህ - ስራህን እናድንቀው! ጥበብህ ሰላምህ - ላ'ለም የሚበቃ ድንቅ፥ መካር፥ ኃያል - የሰላም አለቃ፤ መላእክት ባንድ ላይ - ቅዱስ ነህ ይሉሃል የለም የሚመስልህ - ከሚኖሩት መሃል። [አዝ] ባ'ንተ ያለን ሞኝነት - ከእውቀት ሚዛን ቢጣል ባ'ለም ካሉ ጥበቦች - ብዙ ርቀት ይበልጣል፤ ያ'ንተ ስራ ሲታወጅ - በምድር ላለ አካል ምስጋናህ በህዝብህ ላይ - እንዳ'በባ ይፈካል። [አዝ] ስ'ሰጠን ተመስገን፥ ስታስቀር ተመስገን ያልነውን ነው እንጂ - ያልከውን አትነፍገን፤ ከምናውቅህ በላይ - ስምህ ከፍ ያለ ነው አፍረንብት አናውቅም - አንድ ጊዜም ጠርተነው። በክብርህ የመጡን - እግዚአብሔር ተዋጊ ከቤትህ የጠፉን - እግዚአብሔር ፈላጊ፤ እግዚአብሔር ኃይለኛ - እግዚአብሔር ከፍታ እግዚአብሔር አምባችን - እግዚአብሔር መከታ! እግዚአብሔር - እግዚአብሔር እግዚአብሔር - እግዚአብሔር እግዚአብሔር - እግዚአብሔር እግዚአብሔር - እግዚአብሔር እግዚአብሔር አንተን ነው - ዘውትር የምንጠራው የትኛው ጀግና ነው - አንተን የሚያስፈራው!