Loading
Singer
አዝ፦ ገና ፡ ብዙ (፫x) ፡ ክብር ፡ እናያለን ፡ ቀኑ ፡ ደርሷል የነገው ፡ ዶፍ ፡ ዝናብ ፡ ምልክቱ ፡ ተሸፍኖ ፡ ይሰማናል ወንጌሉ ፡ ጉልበት ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ አይፈራም ፡ የትም ፡ ይገባል ጌታ ፡ ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ያሸንፋል (፪x) መድኃኒት ፡ አለ ፡ እናንተ ፡ ጋር ፡ አድኖ ፡ ፈውሶ ፡ የሚያስቀር መንገዱን ፡ ባካችሁ ፡ አሳዩን ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ መግቢያውን ፡ በር ይሉናል ፡ ይለምኑናል ፡ የሚያቁን ፡ የምናውቃቸው ተፀይፈው ፡ ያባረሩን ፡ ከሰፈር ፡ ከመንደራቸው አዝ፦ ገና ፡ ብዙ (፫x) ፡ ክብር ፡ እናያለን ፡ ቀኑ ፡ ደርሷል የነገው ፡ ዶፍ ፡ ዝናብ ፡ ምልክቱ ፡ ተሸፍኖ ፡ ይሰማናል ወንጌሉ ፡ ጉልበት ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ አይፈራም ፡ የትም ፡ ይገባል ጌታ ፡ ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ያሸንፋል (፪x) የኃጥያት ፡ የችግር ፡ ቀንበር ፡ ተጭኖ ፡ በሰው ፡ ሁሉ ፡ ላይ መታወቂያችን ፡ ርሃብ ፡ ሆነ ፡ ተንቀናል ፡ ዞሮ ፡ እኛን ፡ ላይ የድሆችን ፡ ጩኸት ፡ ሰምቶ ፡ ከሰማይ ፡ ትዕዛዝ ፡ ያወጣል ቸነፈር ፡ ጉስቁልናውን ፡ አባሮት ፡ ጥጋብ ፡ ይጠራል አዝ፦ ገና ፡ ብዙ (፫x) ፡ ክብር ፡ እናያለን ፡ ቀኑ ፡ ደርሷል የነገው ፡ ዶፍ ፡ ዝናብ ፡ ምልክቱ ፡ ተሸፍኖ ፡ ይሰማናል ወንጌሉ ፡ ጉልበት ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ አይፈራም ፡ የትም ፡ ይገባል ጌታ ፡ ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ያሸንፋል (፪x) ከኃጥያት ፡ ጋር ፡ ጨዋታ ፡ ይዘው ፡ በጊዜያዊ ፡ ደስታ ፡ ታለው ክብራቸውን ፡ በነውር ፡ ሸጠው ፡ ፈጣሪያቸውን ፡ እረስተው ገለባ ፡ የሚበላ ፡ እሳት ፡ የመለኮት ፡ ኃይል ፡ ይመጣል አስመሳይ ፡ አታላይ ፡ ሁሉ ፡ ለአንዱ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይሰጣል አዝ፦ ገና ፡ ብዙ (፫x) ፡ ክብር ፡ እናያለን ፡ ቀኑ ፡ ደርሷል የነገው ፡ ዶፍ ፡ ዝናብ ፡ ምልክቱ ፡ ተሸፍኖ ፡ ይሰማናል ወንጌሉ ፡ ጉልበት ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ አይፈራም ፡ የትም ፡ ይገባል ጌታ ፡ ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ያሸንፋል (፪x) ፅድቁ ፡ ሊገለጥ ፡ ማዳኑ ፡ ቀረበ ፡ ከትላንት ፡ ዛሬ የሆታ ፡ ቀን ፡ ሊመጣ ፡ ነው ፡ በምድራችን ፡ ላይ ፡ ዝማሬ በሥሙ ፡ ድንቅና ፡ ተዓምር ፡ ይሰራል ፡ ዝናው ፡ ይወጣል በቤት ፡ ጓዳ ፡ በአደባባይ ፡ ኢየሱስ ፡ አዳኝ ፡ ነው ፡ ይባላል አዝ፦ ገና ፡ ብዙ (፫x) ፡ ክብር ፡ እናያለን ፡ ቀኑ ፡ ደርሷል የነገው ፡ ዶፍ ፡ ዝናብ ፡ ምልክቱ ፡ ተሸፍኖ ፡ ይሰማናል ወንጌሉ ፡ ጉልበት ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ አይፈራም ፡ የትም ፡ ይገባል ጌታ ፡ ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ያሸንፋል (፪x) ጌታ ፡ ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ያሸንፋል (፪x)