Loading
Singer
እኔ ፡ ግን ፡ ሁሉን ፡ ለሚችለው ፡ ለርሱ ፡ ተለይቻለሁ በተቀደሰው ፡ ተራራዬ ፡ ንጉሤን ፡ ሾሜዋለሁ (፪x) አመልከዋለሁ ፡ በቤቴ ፡ አከብረዋለሁ አነግሰዋለሁ ፡ በልቤ ፡ እቀድሰዋለሁ (፪x) ከተነገረለት ፡ ከተባለው ፡ በላይ ትልቅ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ በምድር ፡ በሰማይ እሰግድለታለሁ ፡ ይገባዋል ፡ እሱ ከፍ ፡ አደርገዋለሁ ፡ በቤተ ፡ መቅደሱ ኤልሻዳዩን ፡ አምላክ ፡ ሳመልከው ፡ ከልቤ (፪x) ስሙን ፡ ሳወድሰው ፡ በፍፁም ፡ ሃሳቤ (፪x) ምን ፡ ይሳነዋል ፡ ጌታ ፡ ታምራት ፡ ይሆናል (፪x) የሚገዳደረኝም ፡ ጥሎኝ ፡ ገለል ፡ ይላል አዝ፦ ገለል ፡ ይላል (፫x) ከፊቴ ፡ ገለል ፡ ይላል (፪x) ቢመከር ፡ ቢዶለት ፡ ወጥመድ ፡ ቢዘረጋ የጠላት ፡ ሠራዊት ፡ ሺህ ፡ ሆኖ ፡ ቢንጋጋ እውነት ፡ እንደ ፡ ጋሻ ፡ ዙሪያዬን ፡ ከብቦኝ ምልክት ፡ አለብኝ ፡ በየት ፡ ሊያገኘኝ በነፍሥም ፡ እንኳን ፡ ቢሆንም ፡ እወራረዳለሁ (፪x) ከሚነድም ፡ እሳት ፡ ያድናል ፡ አምናለሁ (፪x) የቃልኪዳን ፡ ልጅ ፡ ነኝ ፡ ይሄው ፡ ነው ፡ ትምክህቴ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ትምክህቴ ጭንገፋና ፡ እርግማን ፡ አይገቡም ፡ በቤቴ (፪x) የጌታን ፡ ሥም ፡ ስጠራ ፡ ችግር ፡ ቢሆን ፡ መከራ ኢየሱስን ፡ ስጠራ ፡ ሸለቆ ፡ ቢሆን ፡ ተራራ የስልጣኑን ፡ ጉልበት ፡ መቼ ፡ ይቋቋማል አዝ፦ ገለል ፡ ይላል ፡ ከፊቴ ፡ ገለል ፡ ይላል (፫x)