Loading
Singer
ገለበጠው ፡ እንጂ ፡ ድንገት ፡ ጌታ ፡ ደርሶ ጠላት ፡ ሲጠባበቅ ፡ ጉድጓድ ፡ ለእኔ ፡ ምሶ ነገር ፡ ሲፈልገኝ ፡ ስፍራ ፡ ለማስለቀቅ በቆፈረው ፡ ጉድጓድ ፡ እራሱ ፡ ገባበት አዝ፦ ዘምር ፡ ዘምር ፡ አለኝ ጠላቴን ፡ ጥሎ ፡ ስላሳየኝ (፪x) እነኛ ፡ በፈረሳቸው ፡ በሚያልፈው ፡ ነገር ፡ ታመኑ በሰረጐቻቸው ፡ ብዛት ፡ እጅጉን ፡ ተገዳደሩ ግን ፡ እንደዋዛ ፡ አለፉ ፡ ተሰነቃቅለው ፡ ወደቁ የእኔ ፡ ግን ፡ መተማመኛ ፡ አሁንም ፡ አለ ፡ በክብሩ አዝ፦ ዘምር ፡ ዘምር ፡ አለኝ ጠላቴን ፡ ጥሎ ፡ ስላሳየኝ (፪x) በንጉሥ ፡ ደጃፍ ፡ ተጥዬ ፡ ሃማ ፡ ግልምጫው ፡ በርትቶ ስገድ ፡ ሲለኝ ፡ አልሰግድም ፡ ምንም ፡ ቢያይ ፡ ተቆጥቶ እጄን ፡ አልሰጥም ፡ ለጠላት ፡ ክፉ ፡ ደግ ፡ በእኔ ፡ ቢያወራ ቀን ፡ ቆጥሮ ፡ አምላኬ ፡ ይመጣል ፡ ታሪክን ፡ በእኔ ፡ ሊሰራ አዝ፦ ዘምር ፡ ዘምር ፡ አለኝ ጠላቴን ፡ ጥሎ ፡ ስላሳየኝ (፪x) ጠላት ፡ ቢፎክር ፡ ቢያቅራራ ፡ አዋጅ ፡ ቢታወጅ ፡ በእኔ ፡ ላይ ከቶ ፡ እንዳሰበው ፡ አይሆንም ፡ አምላኬ ፡ እኮ ፡ አለ ፡ በሰማይ አዋጅን ፡ በአዋጅ ፡ ገልብጦ ፡ ጌታ ፡ መጣና ፡ ቀደመው ነገሩ ፡ ተገለበጠ ፡ ጠላት ፡ ገባ ፡ በቆፈረው ገለበጠው ፡ እንጂ ፡ ድንገት ፡ ጌታ ፡ ደርሶ ጠላት ፡ ሲጠባበቅ ፡ ጉድጓድ ፡ ለእኔ ፡ ምሶ ነገር ፡ ሲፈልገኝ ፡ ስፍራ ፡ ለማስለቀቅ በቆፈረው ፡ ጉድጓድ ፡ እራሱ ፡ ገባበት አዝ፦ ዘምር ፡ ዘምር ፡ አለኝ ጠላቴን ፡ ጥሎ ፡ ስላሳየኝ (፪x)