Loading
Singer
ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቆልፎባቸው ፡ ኤሄሄ ፡ ኤሄሄ ፡ ኤሄዉ የፈርዖን ፡ ሠራዊት ፡ የሚያንገላታቸው አሉ ፡ የተገፉ ፡ ስምህን ፡ ለማስከበር ፡ ኤሄሄ ፡ ኤሄሄ ፡ ኤሄዉ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ገርስሰው ፡ የጠላትን ፡ መንደር (፪x) አዝ፦ ስለ ፡ ሥምህ ፡ ተጠልተው ፡ ያሉትን ፡ በሰንሰለት (፪x) አብራላቸው ፡ ክብርህን ፡ ጋርዳቸው ፡ ከመታከት ግንባራቸው ፡ ይጠንክር ፡ ጠላታቸው ፡ ይርበትበት ለሥምህ ፡ ነዉና ፡ ልጆችህን ፡ አጽና አንተን ፡ እንዲክዱ ፡ ባንተ ፡ እንዲያማርሩ ፡ ኡሁሁ ፡ ኡሁሁ ፡ ኡሁዉ ይሸርባል ፡ ጠላት ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ምስጢሩ ምሬት ፡ በሕይወታቸው ፡ እንዳይሆን ፡ ጋርዳቸው ፡ ኤሄሄ ፡ ኤሄሄ ፡ ኤሄው ፈቃድህ ፡ ይፈፀም ፡ እንድትከብርባቸው (፪x) አዝ፦ ስለ ፡ ሥምህ ፡ ተጠልተው ፡ ያሉትን ፡ በሰንሰለት (፪x) አብራላቸው ፡ ክብርህን ፡ ጋርዳቸው ፡ ከመታከት ግንባራቸው ፡ ይጠንክር ፡ ጠላታቸው ፡ ይርበትበት ለሥምህ ፡ ነዉና ፡ ልጆችህን ፡ አጽና ጠላትም ፡ ይንቀጥቀጥ ፡ ይታሰር ፡ ምላሱ ፡ ኡሁሁ ፡ ኡሁሁ ፡ ኡሁዉ ይተብተብ ፡ እጅ ፡ እግሩ ፡ ይቅር ፡ መላወሱ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ይመስክር ፡ ስለ ፡ ኃያልነትህ ፡ እሂሂ ፡ እሂሂ ፡ እሂ ይሳቁ ፡ በፈርዖን ፡ ድል ፡ ያርጉ ፡ ልጆችህ (፪x) አዝ፦ ስለ ፡ ሥምህ ፡ ተጠልተው ፡ ያሉትን ፡ በሰንሰለት (፪x) አብራላቸው ፡ ክብርህን ፡ ጋርዳቸው ፡ ከመታከት ግንባራቸው ፡ ይጠንክር ፡ ጠላታቸው ፡ ይርበትበት ለሥምህ ፡ ነዉና ፡ ልጆችህን ፡ አጽና ከእንግዲህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ፀሎታችን ፡ ስማ ፡ አሀሀ ፡ አሀሀ ፡ አሀ ታምነናል ፡ በኃይልህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አንተማ እንክትክት ፡ ብለዉ ፡ የወህኒ ፡ መዝጊያዎች ፡ ኦሆሆ ፡ ኦሆሆ ፡ ኦሆች ያመልኩሃል ፡ በክብር ፡ በድል ፡ ያንተ ፡ ልጆችህ (፪x) አዝ፦ ስለ ፡ ሥምህ ፡ ተጠልተው ፡ ያሉትን ፡ በሰንሰለት (፪x) አብራላቸው ፡ ክብርህን ፡ ጋርዳቸው ፡ ከመታከት ግንባራቸው ፡ ይጠንክር ፡ ጠላታቸው ፡ ይርበትበት ለሥምህ ፡ ነዉና ፡ ልጆችህን ፡ አጽና (፪x)