Loading
Singer
አዝ፦ ተስፋ ፡ አለው ፡ ፊትህን ፡ ሳየው በረታሁ ፡ ፊትህን ፡ ሳየው ደስታ ፡ አለው ፡ ፊትህን ፡ ሳየው ተጽናናሁ ፡ ፊትህን ፡ ሳየው (፬x) አቅም ፡ አጥቼ ፡ ጉልበት ፡ ሲላላ እምነቴ ፡ ጠፍቶ ፡ ሳይ ፡ ወደኋላ (፪x) አሁንስ ፡ ተስፋዬ ፡ ማነው ፡ ብዬ ከአፌ ፡ ሳልጨርስ ፡ መጣህ ፡ አባብዬ ከፊትህ ፡ ጋር ፡ ደስታን ፡ አጠገብከኝና ላመሰግንህ ፡ ቆምኩ ፡ እንደገና (፪x) ላመሰግንህ ፡ እንደገና ፡ ላመሰግንህ ፡ ቆምኩ ፡ እንደገና ላመሰግንህ ፡ እንደገና ፡ ላመሰግንህ ፡ ቆምኩ ፡ እንደገና አዝ፦ ተስፋ ፡ አለው ፡ ፊትህን ፡ ሳየው በረታሁ ፡ ፊትህን ፡ ሳየው ደስታ ፡ አለው ፡ ፊትህን ፡ ሳየው ተጽናናሁ ፡ ፊትህን ፡ ሳየው (፪x) በመተማመን ፡ የጠበቀህ ፡ ሰው የሚጐበኝበት ፡ ቀኑ ፡ ቢርቀው (፪x) በምትዘገይ ፡ ተስፋ ፡ እንዳያዝን ፡ ልቡ ፈጥነህ ፡ ትደርሳለህ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ፡ አምላኩ ከፊትህ ፡ ጋር ፡ ደስታን ፡ አጠገብከኝና ላመሰግንህ ፡ ቆምኩ ፡ እንደገና (፪x) ላመሰግንህ ፡ እንደገና ፡ ላመሰግንህ ፡ ቆምኩ ፡ እንደገና ላመሰግንህ ፡ እንደገና ፡ ላመሰግንህ ፡ ቆምኩ ፡ እንደገና አዝ፦ ተስፋ ፡ አለው ፡ ፊትህን ፡ ሳየው በረታሁ ፡ ፊትህን ፡ ሳየው ደስታ ፡ አለው ፡ ፊትህን ፡ ሳየው ተጽናናሁ ፡ ፊትህን ፡ ሳየው (፬x)