Loading
Singer
ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ፡ ያበራል እንደብዙ ፡ ውሆች ፡ ድምጽህም ፡ ያስፈራል ግርማህ ፡የደመቀ ፡ ሞገስህ ፡ ልዩ ፡ ነው እግርህ ፡ ስር ፡ ወድቄ ፡ እሰግድልህ ፡ አለሁ አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ የዘለዓለም ፡ ጌታ ሞትን ፡ ድል ፡ ያደረክ: ኃጢአትን ፡ የረታህ ከወገን ፡ ከቋንቋ ፡ህዝቦችን ፡ የዋጀህ ለአምላክህ ፡ መንግሥት ፡ ካህናት ፡አድርገህ (ሰባቱን ፡ መጽሃፍት፡ ማህተም ፡ የፈታ ውበትህ ፡ ያማረ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ) (፪x) አዝ ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ምስኪን ፡ ሆነህ ፡ መተህ ፡ ምስኪኑን ፡ ያከበርክ ደሃ ፡ ሆነህ ፡ መተህ ፡ ደሃን ፡ ያበለጸክ በደዌ ፡ ተመተህ ፡ ህምሙን ፡ የፈወስክ ኃጢአትን ፡ ለብሰህ ፡ ሃጢያኑን ፡ ያነጻህ (ድል ነስተህ ፡ በኃይልህ ፡ ባለድል ፡ ያረከን አንተ ፡ አትጠገብም ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን) (፪x) አዝ ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ማምለጫ ፡ ቀዳዳ ፡ መሹለኪያ ፡ ሲጠፋ ጐዳናው ፡እጅግ ፡ ጠቦ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲጋፋ ችግር ፡ መፍታት ፡ አንተ ፡ ልማድህ ፡ ነውና መጽሃፉን ፡ ገልጽህ ፡ ማኅተሙን ፡ ፈታህ ጌታችን ፡(ኢየሱስ) ፡ ተባረክ ፡ ባለግርማ ፡ ሞገስ ዙፋንህ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ በዓለም ፡ ሁሉ ፡ ንገሥ አዝ ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ